በአሰልጣኝ ዮሐሃንስ ሳህሌ እየተመራ 11 ተጨዋቾችን ያስፈረመው ድሬዳዋ ከተማ ዮናታን ከበደን ከወላይታ ድቻ የክረምቱ 12ኛ ፈራሚውን ኣድርጓል።ባለፈው ዓመት ከወላይታ ድቻ ጋር ያሳለፈው የቀድሞው የአርባምንጭ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋች ዮናታን መቐለ ላይ ዝግጅቱን በማድረግ ላይ ሚገኘውን የድሬዳዋ ከተማ በመቀላቀል ነገ በሚጀመረው ትግራይ ዋንጫ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል።
ሀይሉ ነጋሽ፣ኢታሞና ኮሚኔን፣ምንተስኖት የግሌን ጨምሮ 9 ተጨዋቾችን ያስፈረመው ድሬዳዋ እንደ ኣዲስ እየተዋቀረ ያለውን ቡድን የማቀናጀት ከፍተኛ ስራ ይጠብቃቸዋል፤ እንዲረዳቸው ትግራይ ዋንጫም ኣቋሟቸውን ሚፈትሹበት ጥሩ ኣጋጣሚ ሆኖላቸዋል።