በመቐለ 70 እንደርታ እሸናፊነት በተጠናቀቀው የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከሊጉ የወረደው ደደቢት ቀጣይ ዓመት በመሰቦ ስር ሆኖ በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ይሆናል።
ባለፋት ዓመታት ከተለያዩ ከድርጅቶች በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ በፕሪምየር ሊጉ ከጥሩ ተፎካካሪነት ባሻገር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እስከ ማንሳት ደርሶ የነበረው ደደቢት በተጠናቀቀው የውውድር ዓመት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እስከ መፍረስ ደርሶ እንደነበር ሚታወስ።
መሉ ርክክቡን በሚመለከት በቀጣይ ቀናት ክለቡ ጋዜጣዊ መግለጫ ሚሰጥ ይሆናል።