ደደቢት እግር ኳስ ክለብ በ3 ተጫዋቾቻው ላይ ከዲስፕሊን ጉድለት ጋር በተያያዘ ያሳለፉትን የቅጣት ውሳኔን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔው አሰተላልፏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የክለቡ ተጨዋቾች በሆኑት ዳዊት ፍቃዱ ፤ሳምሶን ጥላሁን እና አክሊሉ እንየው ለክለቡ ያቀረቡት የይቅርታ ደብዳቤ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ምክንያት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ነሀሴ 03 ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሜቴ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ይህንን ተከትሎም ዲሲፕሊን ኮሚቴው ደደቢት 3 ተጫዋቾቹ ላይ የጣለው የቅጣት ውሳኔ አላሳመንኝም እና የቅጣት ውሳኔውን ሽሬ ተከታዩን ውሳኔ ወሰኝኛለው ብሏል፡፡
በዚህም መሰረት ደደቢት ለተጫዋቾቹ አሁንም መልቀቂያ ለመስጠት ፍቃደኛ አለመሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለሳምሶን ጥላሁን ፣ ለዳዊት ፍቃዱ እና አክሊሉ እንየው የመልቀቂያ ደብዳቤ እንደሚጽፍ እና ከዚህ ቀደም ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ተጫዋቾች ላይ የተወሰነውን ደደቢት እግርኳስ ክለብ ተጫዋቾች ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ እንደሻረ አሳውቋል፡፡