ደደቢት እግር ኳስ ክለብ የጣሊያኑ የትጥቅ አምራች ኢርያ ምርት የሆነውን አዲሱን ትጥቅ ዛሬ በሞናርክ ሆቴል በይፋ አስተዋወቀ።
ክለቡ ከኢሪያ ተወካይ ሚስተር ካርሎ ከደደቢት አስኪያጅ አቶ ሚኬኤሌ አምደመስቀል ጋር የሶስት አመት የማሊያ አቅርቦት እና ስፖንሰርሺፖ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የትጥቅ ግዢው የደደቢት ዋና ማልያ እና ተለዋጭ ማልያን ያካተተ ሲሆን በተጨማሪም ልምምድ መስሪያ፣ የአሰልጣኞች ትጥቅ፣ ኳሶችን እና የመሳሰሉትንም ያካተተ ነው።
የስፓንሰር እና የትጥቅ አቅርቦት ስምምነቱ ለ 3ዓመት የሚቆይ ሲሆን ደደቢት በጥራት ተጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር በየዓመቱ ለትጥቅ ከሚያወጣው 50 በመቶ ማዳን ይችላል በማለት የተናገሩት አቶ ሚኬኤሌ አምደመስቀል ናቸው፡፡
የጣሊያኑ የትጥቅ አምራች ኩባኒያ ኤሪያ ከትጥቅ ማቅረቡ በተጨማሪ ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎችን እንደሚያደርግ በተወካዮ በሚስተር ካርሎ ተጠቅሷል ፡፡
በመጨረሻም የክለቡ የወንድ እና ሴት ተጫዋቾች ማሊያውን በመልበስ ለጋዜጠኞች አስተዋውቀዋል፡፡