በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ሚሆኑት ደደቢቶች የክረምቱ 11ኛ ፈራሚያቸውን ዲሜጥሮስ ወልደስላሴ አድርገዋል።
ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከስሑል ሽረ ጋር በስምምነት የተለያየው ዲሜጥሮስ ማረፍያውን ሰማያዊዎቹ በማድረግ የጌታቸው ዳዊትን ስብስብ ተቀላቅሏል።የቀድሞው የአዳማ ከተማ ና የአዲስ አበባ ከተማ ተጨዋች ዲሜጥሮስ ደደቢት በተካላካይ ክፍል ያለውን የተጫዋች አማራጭ ሊያሰፋላቸው እንደሚችል ይገመታል።
የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በመቐለ እያደረጉ ሚገኙት ደደቢቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት በሽቶ ሚድያ ፕሮዳክሽንና በትግራይ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትብብር በሚዘጋጀው ትግራይ ዋንጫ ላይ ሚሳተፋ ይሆናል።