ድሬዳዋ ከተማ አጥቂ ስፍራ ላይ ለሚጫወተው ዳኛቸው በቀለ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
የክለቡ ፌስ ቡክ ገፅ እንደሚያመላክተው። ተጫዋቹ በተደጋጋሚ የመሰለፍ እድል የተሰጠው ቢሆንም ከአቅም በታች በመጫወቱ ከዚህ በፊትም በአሰልጣኞች የቃል ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲሆን ለቡድኑ መስጠት ካለበት አገልግሎት አንፃር ድክመት ስለታየበት በቀጣይ ይህን እንዲያስተካክል ክለቡ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል። ከዚህ በኋላ ተጫዋቹ አቋሙ የማያስተካክል ከሆነ በውሉ መሰረት ክለቡ አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቋል። ክለቡ ከዚህ ቀደም ለናይጄሪያዊው አጥቂ ባድዋ አደግሰን የፅሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ አይዘነጋም።