ድሬዳዋ ከተማ አሰልጣኝ ስምኦን አባይን አሰናበተ።
የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንዳስታወቀው ክለቡ አሰልጣኙን ለማሰናበት የተገደደው በዚህ አመት ክለቡ ያስቀመጠላቸው ቅድመ ሁኔታወች ማሟላት ባለመቻሉ መሆኑን ጠቅሷል። አሰልጣኙ በክለቡ ለተከታታይ 3 አመታት የቆዩ ሲሆን። ሁለት ግዜ በተመሳሳይ ዋና አሰልጣኞች ሲሰናበቱ ክለቡን በመረከብ ማሰልጠን ችለዋል። ክለቡም በምክትል አሰልጣኝ ፍስሀ ጡዑመልሳን በጊዚያዊነት የሚመራ ሲሆን። ጊዚያዊ አሰልጣኙ ከስሁል ሽረ ጋር ባላቸው ጨዋታ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ድሬዳዋ በ13 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።