የኢትዮጵያ አሸናፊ የነበረው ስመ ገናናው ጥጥ ማህበር/ ኮተን/ ለመጀመሪያ ግዜ ከኢትዮጵያ ወደ ጋና አቅንቶ አሻንቲ ኮቶኮን በገጠመበት ቢሸነፍም በመጀመሪያ ተሳትፏችን በአፍሪካ እግር ኳስ ታሪክ የማይረሳ አሻራውን ቡድኑ ባሳረፈበት ወቅት የቡድኑ አባል የነበረ ሁለት ቁጥር መለያ በመልበስ በተከላካይ ስፍራ በመጫወት እየተምዘገዘገ ኳስን ያወጣ ስለነበር ከመታወቂያ ስሙ ይልቅ ድራጎን በመለው ስሙ ገኖ ይታወቅ የነበረው ድሬዳዋ ያፈራችው መሀመድ ኡስማን በሳለፍነው አርብ ጥር 8/2012 አርፏል።
መሀመድ ኡስማን በ4ኛው እና 5ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያን በመወከል በወቅቱ ከነበሩት ዝነኞች ሉቿባ ሳሎን እና ኢታሎ ባሳሎ ተጫውተዋል። ለሀረርጌ ምርጥ የተጫወተ ሲሆን። አግር ኳስ ካቆመ በኃላ የአሰልጣኝነት ስልጠና ጀርመን ሀገር በመውሰድ በአንድ ወቅት የሶማሊያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጥኗል። በመሀመድ ኡስማን (ድራጎን) የተሰማትን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቹ ወዳጅ አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን