በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በርካታ ተጨዋቾቹን ያጣው ድሬዳው አራት ተጨዋቾችን ማስፈረም ችሏል።
ሳሙኤል ዮውሃንስን ለወልዋሎ አሳልፈው የሰጡት ድሬዎች ዘካርያስ ቱጂን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ አስፈርመዋል።የፈረሰኞቹ አካዳሚ ውጤት የሆነው ዘካርያስ ቱጂ ሳሙኣል ዬውሃንስ ትቶት የሄደውን ክፍተት ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል።
አማኑኤል ተሾሙ ሌላኛው ድሬዳዋን የተቀላቀለ ተጨዋች ነው።ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከመከላከያ ጋር ያሳለፈው አማኑኤል ተሾመ ሚኪያስ ትቶት የሄደውን ቦታ ሚሸፍን ይሄናል።
- ማሰታውቂያ -
ሥስተኛው የድሬዳዋ ፈራሚ ዋለልኝ ገብሬ ከጅማ ኣባቡና ሆኗል።በግማሽ ዓመት የዝውውር መስኮት ወልዋሎን በመልቀቅ ጅማ አባጅፋርን የተቀላቀለው ዋለልኝ ገብሬ ከ6 ወራት ቆይታ በኃላ ጅፋሮችን በመልቀቅ ድሬዳዋ ከተማን መቀላቀል ችሏል።
አራተኛው ፈራሚ ተከላካዩ ዘሪሁን አንሼቦ ከደቡብ ፖሊስ ሆናል።በዘንድሮው የውድድር ዓመት ከደቡብ ፖሊስ ጋር ወደ ከፍተኛ ሊጉ የወረደው ዘሪሁን አንሼቦ በአንድ ዓመት ውል የቀድሞ ክለቡን ድሬዳዋ ከተማን ተቀላቅሏል።