ባሳለፍነው ሳምንት በርካታ ተጨዋቾችን በማስፈረም ወደ ዝውውሩ የገቡት ጅማ አባጅፋሮች ጀሚል ያቆብን አስፈርመዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በከፍተኛ ሊጉ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያሳለፈው የቀድሞው የጅማ አባቡና ተጨዋች ጀሚል ያቆብ በግራ ና በቀኝ መስመር ተከላካይነት በመጫወት ይታወቃል።
በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ለመቀላቀል ተስማምቶ የነበረው ጀሚል ያቆብ በመጨረሻ ማረፍያው አባጅፋሮችን አድርጓል።በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን ለመቀላቀል ተስማምቶ ከወልዋሎ ጋር ልምምድ ማድረግ ጀምሮ የነበረው ጀማል ያቆብ በመጨረሻ ማረፍያው አባጅፋሮችን አድርጓል።