በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር
የስድስት ተጨዋቾችን የኮንትራት ስምምነት አራዝሞ 11 አዳዲስ ተጨዋቾችን ያስፈረመው ጅማ አባ ጅፋር ወደ ኢስማኤልያ እና መቀሌ ከነማ እንዳመራ ሲነገር የቆየውን የአጥቂውን ኦኪኪ አፎላቢ ኮንትራት እንዳራዘመ የክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ዘግቧል፡፡ ግብ ጠባቂው ዳንኤል አጄ እና ተከላካዩ አዳማ ሲሶኮ ሌሎች ኮንትራተታቸውን ያራዘሙ የክለቡ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ የወቅቱ የፕርሚየር አሸናፊ ክለብ የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅቱን በቀጣዩ ሳምንት በአዳማ ይጀምራል፡፡
ጅማ አባ ጅፋር የኦኪኪን ኮንትራት ስምምነት አራዝሟል
Managing Editor at Hatricksport Website