“በወርቃማው ዕድል ብደሰትም የጊዜው ማጠር ስጋትን ፈጥሮብኛል”
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
አለም አቀፍ ግንኙነቷና ተመራ
ጭነቷ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ
የመጣው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ
ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ
አለም በጉጉት በሚጠብቀውና የምድራችን
ምርጥ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች የኮኮብ
ምርጫ ላይ እንዲገኝ ከአለም የእግር ኳሱ
የበላይ አዛዥ ከሆነው ፊፋ የግብዣ ጥሪ
ቀረበለት፡፡
ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ የአገር
ውስጥ ስፖርት አፍቃሪዎች የመረጃ
ጥማትን የማርካት መርህ በማንገብ
እንቅስቃሴ በመጀመር አሁን ላይ ነጥረው
ከቀሩት ጥቂት ጋዜጦች መካከል አንዷና
ብቸኛዋ ባለቀለምና እንደዚሁም በዘመናዊ
ቅርፅ በመምጣት ረገድ ፈር ቀዳጅ ለመሆን
የበቃችው ሀትሪክ ጋዜጣ ከዓመታቶች
በፊት የጀመረችው ዓለም አቀፍ ግንኙነት
የፈጠረላት ተመራጭነት እየሰፋ በመምጣቱ
ልምዷንና ተሞክሮዋን የበለጠ እያዳበረች
እንድትጓዝ ያበቃት መሆኗን የገለፀው
ማኔጂንግ ኤዲተሩ ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ
የዓለም ኮከቦች ምርጫ ላይ እንዲገኙ
ከተጋበዙ የዓለማችን ታዋቂ የስፖርት
ጋዜጠኞች መካከል ፊፋ ዕድሉን በክብር
እንደሰጠው ገልጿል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የፊፋ
የዓለም ኮከቦች ምርጫ ላይ ሀትሪክን
በመወከል በየዓመቱ በምርጫው
በመሳተፍ ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛው
ኦክቶበር 23 ቀን በሚደረገው
የ2017 የአለም ኮከብ ተጨዋቾች
ምርጫ ለንደን ተገኝቶ እንዲታደም
መጋበዙ ለጋዜጣዋ ዝግጅት ክፍል
አባላት ብቻ ሣይሆን ለአንባቢዎቿና
ለመላው ስፖርት ጋዜጠኞች እንደ
ተጨማሪ ስኬት ሊቆጠር የሚገባው
መሆኑን ገልጿል፡፡
ክርስቲያኖ ሮናልዶ፣ ሊዮኔል
ሜሲ እና ኔይማርን የመሳሰሉ
የዓለማችን የእግር ኳስ ከዋክብትንና
እንደዚሁም ጆዜ ሞውሪንሆ፣ ዚነዲን
ዚዳን፣ ፔፕ ጋርዲዮላን ጨምሮ
ታላላቅ አሰልጣኞችና ጋዜጠኞች
በሚገኙበት የለንደኑ የዓለም ኮከብ
ተጨዋቾችና አሰልጣኞች ምርጫ
ላይ የሚሳተፈው ጋዜጠኛ ይስሐቅ
በላይ ፕሮግራሙ በሚካሄድበት
“London Palladiun Theatre
Argyll Street” እንዲገኝ የግብዣው
ጥሪ እንደደረሰው በመግለፅ የለንደንን
ቪዛ በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል
ጋር ግንኙነት ለመጀመር ኢ-ሜይል አድርጎ
መልስ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡
“ይህንን መሰሉ ዕድል ስለመጣልኝ እንደ
አንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ኩራትና መነሳሳት
ፈጥሮልኛል፤ ስኬቱ የአንባቢዎቻችንና
የሁላችንም ነው” ያለው ጋዜጠኛ ይስሐቅ
ግብዣው ከመጣ በኋላ ወደ ስፍራው ለመጓዝ
ያለው ጊዜ አጭር ቢሆንም ወርቃማውን
እድል በመጠቀም በስፍራው ለመገኘት
እስከ መጨረሻው ጥረት እያደረገ መሆኑን
አስታውቋል፡፡ “በለንደን የቪዛ ህግ መሰረት
በመደበኛ ሁኔታ ቪዛ ለማግኘት 15 የስራ
ቀናትን የሚጠይቅ ሲሆን በአስቸኳይ ደግሞ
ተጨማሪ ክፍያ ተከፍሎ ቪዛ ለማግኘት 10
የስራ ቀናትን መጠየቁ ወርቃማው ዕድል
እንዳያመልጠኝ ስጋት ፈጥሮብኛል” የሚለው
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በዚህ የዓለማችን
ታላቅ የኮከቦች ምርጫ ላይ ለመገኘት
አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ እንደሚያደርግ
ገልፆ የዓለም እግር ኳስ የበላይ አዛዥ የሆነው
ፊፋ ለሀትሪክ ጋዜጣና ለማኔጂንግ ኤዲተሩ
ክብርና ዕውቅና ሰጥቶ ከሌሎች ታላላቅ
የዓለማችን ጋዜጠኞች ዕኩል በስነ-ስርዓቱ
ላይ እንዲገኝ መጋበዙ እንደ ሀገርም እንደ
ሚዲያ የሚያኮራና ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳ
መሆኑን ደግሞ ገልጿል፡፡
ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ ዘንድሮ
ለጋዜጠኞች በተሰጠው ዕድልና በተላከለት
ፎርም መሰረት በፊፋ የ2017 ምርጥ
የሴት ተጨዋቾች ምርጫ ላይ በመሳተፍ
“የእኔ የዓመቱ ምርጦች ናቸው” ያላቸውን
ተጨዋቾች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለው ደረጃ
ይገባቸዋል በማለት ምርጦቹን መርጦ
ያሳወቀ ሲሆን፤ በዚህም
1ኛ. Lloyd Carly (USA)/Houston
Dash/Man.City,
2ኛ. Marozsan Dzsenifer
(Germany)/ Olympic Lyonnais,
3ኛ. Kerr Sam (Australia)/ Perth
Glory/Sky Blue FC፤
በሴት አሰልጣኞች ደግሞ
1ኛ. Kellermann Ralf (Germany)/
Wolfsburg
2ኛ. Precheur Gerard (France)/
Olympic Lyonnais,
3ኛ. Hayes Emma (England)/
Chelsea ለተባሉት ተጨዋቾችና አሰልጣኞች
ኢትዮጵያን ወክሎ ድምፁን የሠጠ ሲሆን
አሸናፊዎቹ በለንደን በሚዘጋጀው የኮከቦች
ምርጫ ላይ በይፋ የሚታወቁ ይሆናል፡፡
ዓለም አቀፍ ግንኙነቱ ከጊዜ ወደ
ጊዜ እያደገ የመጣው የሀትሪክ ጋዜጣ
ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ
እ.ኤ.አ በ2008 ዓ.ም በተደረገው የቤጂንግ
ኦሎምፒክ በአካል በመገኘት የጀመረው
ኢንተርናሽናል ተሳትፎውን በመቀጠል
በ2010 በደ/አፍሪካው የአለም ዋንጫ፤
በ2011 የጀርመኑ የሴቶች የአለም ዋንጫ
(በብቸኝነት)፣ በ2012 በፖላንዱ የአውሮፓ
ዋንጫ የዝግጅት ሂደት ጉብኝት ላይ፣ በ2013
የደ/አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ፣ በ2015
የካናዳ የሴቶች የዓለም ዋንጫ (በብቸኝነት)፣
በ2017 በካናዳ የወርቅ ደረጃ ባለው የኦታዋ
ማራቶንን (በብቸኝነት)፣ በ2017 የለንደኑን
16ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ
በመሳተፍ ለአንባቢዎቻችን ወቅታዊና ሰፋፊ
ዘገባዎች ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
ዝግጅት ክፍሉን በመወከል በአካል
ለመታደም በመብቃት በ2010 የአለም
ዋንጫ ፈረንሣዊውን አሰልጣኝ አርሴን
ቬንገርን በአካል አግኝቷቸው ለደቂቃዎች
ለማነጋገርና በምስል ለማስቀረት የበቃው
ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ በለንደኑ የአለም
አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በተገኘበት ወቅት
የአርሴናልንና የሌሲስተር ሲቲን የሲዝኑን
የመክፈቻ ጨዋታ በኤምሬትስ ስቴዲየም
ተገኝቶ ከመከታተሉም ባሻገር የኤምሬትስና
የስታምፎርድ ብሪጅ ስታዲየሞችን
በመጎብኘት ወደ አገሩ መመለሱ አይዘነጋም፡፡