በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር በንቃት እየተሳተፋ ሚገኙት ጌዲኦ ዲላዎች የአምስት ነባር ተጨዋቾቻቸውን ውል ሲያራዝሙ ታምሩ ባልቻን ከኢኮስኮ አስፈርመዋል።
በተጨማሪ የአጥቂ መስመር ተጨዋች የሆነው ምትኩ ጌታቸውን ከአርሲ ነገሌ፣ግብ ጠባቂ ታደሰ ያለው ከድሬዳዋ ፖሊስ ማስፈረም ችለዋል።
ብሩክ ግርማ፣ሳሙኤል ቦጋለ፣ፋሲል አበባየሁ፣ዘመርኩን ሽክሮ እና ቢንያም በቀለ ከጌዲኦ ዲላ ጋር ሚያቆያቸውን የአንድ ዓመት በመፈረም ለቀጣይ ውድድር ዓመት ከክለቡ ጋር ለመቀጠል የተስማሙ ተጨዋቾች ናቸው።