ባሳለፍነው ማክሰኞ ባህርዳር ከተማ በሜዳው ከደቡብ ፖለስ ጋር እቻ መለያየቱን ተከትሎ ከደጋፊዎች በደረሰባቸው ተቃውሞ ምክንያት ከጨዋታው በኃላ ከእሰልጣንነታቸው ራሳቸው ማንሳታቸውን ገልፀው የነበሩት ጳውሎስ ጌታቸው ወደ ስራቸው መመለሳቸው ታውቋል።
ዛሬ ስብሰባ ያደረገው የባህርዳር ከተማ ቦርድ የተጨዋቾችን ፍላጎት በመጠየቅ የነበሩት ችግሮችን በመፍታት ጳውሎስ ጌታቸው ወደ ስራው እንዲመለስ እድርገዋል።
33 ነጥቦችን በመያዝ 6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ባህርዳር ከተማ በመጀመርያ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዓመት ተሳትፏቸው እያሳዩ ሚገኙት ብቃት እሚበረታታና ያልተገመተ ነው።