በ2018ቱ የቶታል ካፍ ሻምፒዬንስ ሊግ እየተሳተፉ የሚገኙት ፈረሰኞቹ በመጀመሪያው ዙር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሱዳኑን አልሰላም ዋኡ በፎርፌ በማሸነፍ ከዩጋንዳው ካምፓላ ሲቲ (ኬሲሲኤ) ጋር መገናየታቸው ይታወቃል፡፡
ፈረሰኞቹ ተጋጣሚያቸውን ካምፓላ ሲቲ (ኬሲሲኤ) ባለፈው ሳምንት በሜዳቸው አዲስ አበባ ስታዲዬም በገጠሙበት ጨዋታ ያለ ግብ መለያየታቸው የሚታወስ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ ለማድረግ ዛሬ ረፋድ 4:05 ከቦሌ አየር መንገድ ወደ ዩጋንዳ ኢንቴቤ አየር መንገድ ያመሩ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት መድረሳቸው ታውቋል፡፡
የፈረሰኞቹ ልዑካን ቡድን ኤንቴቤ አየር መንገድ ሲደርስ በርካታ ዩጋንዳዊያን ለግብ ጠባቂው ሮበርት ኦዶንካራ አቀባበል ከማድረጋቸውም ባሻገር የሬድዮና የቴሌቪዥን ባለሙያዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በፈረሰኞቹ ልዑካን ቡድን ስብስብ በጉዳት ምክንያት የፊት መስመሩ ንጉስ ሳላዲን ሰይድ አለመጓዙ ተነግሯል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ፈረሰኞቹ ከኢንቴቤ አየር መንገድ፡ተነስተው ጨዋታው ወደሚደረግበት ወደ ዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ እያመሩ ነው፡፡
የዩጋንዳ የቀኑ የአየር ሁኔታ ከፊል ዝናባማ እና ጭጋጋማ መሆኑን የሜትሮሎጂ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
photo credit-st george page