በበርካታ ደጋፊዎቻቸው ታጅበው ያደረጉት
ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 3ለ2 አሸናፊነት
ተጠናቋል፡፡ ሳሙኤል ሳኑሚ፣ ኤልያስ
- ማሰታውቂያ -
ማሞና አቡበከር ናስር ለቡና ኤርሚያስ
ሃይሉና መሃመድ ናስር ለፋሲል ጎሎቹን
አስቆጥረዋል፡፡ የ2009 ምስጉን ዳኛ
ተብሎ የተመረጠው ኢንተርናሽናል
አርቢትር አማኑኤል ሃ/ስላሴ የመራው
ጨዋታ ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳ ሲሆን
ፋሲሎች በዳኛው ውሳኔ በመበሳጨት
የክስ ሪዘርቭ ማስያዛቸው ታውቋል፡፡
የጨዋታው መጠናቀቅ ተከትሎ የቡናው
ምክትል አሰልጣኝ መሃመድ ኢብራሂም
(ኪንግ) “ዳኞችን መውቀስና መተቸት
አልፈልግም ባላቸው አቅም እየሰሩ
እንደሆነ አውቃለሁና” ሲል የፋሲሉ
ምንተስኖት ጌጡ በበኩሉ “ኢትዮጵያ
ቡና አላሸነፈንም ያሸነፈን ዳኛው ነው፡
፡ 75 በመቶ የተሸነፍነው በዳኛው ነው
የሚመለከተው አካል ርምጃ መውሰድ
አለበት፡፡ አገርን ወክለን ነው የመጣነው
ብዙ ሃብት ባክኗል ውጤት ለማስለወጥ
የሚሞክር ከሆነ ባንለፋ ይሻላል” ሲሉ
አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ ዳኝነት ከስህተት
የፀዳ ባለመሆኑ ጎንደር ላይ ፋሲል
ኤሌክትሪክን 1ለ0 በረታበት ጨዋታ
የኤሌክትሪኩ አልሃሰን ካሉሺያ ተጠልፎ
የመሃል ዳኛው ሳህሉ ይርጋ በዝምታ
ማለፋቸውን ተከትሎ ኤሌክትሪኮች የክስ
ሪዘርቭ ማስያዛቸውን የሚያወሱ ወገኖች
የፋሲሎች ቁጣ ተጋኗል ባይ ናቸው፡፡
የአርቢትር አማኑኤል ሃ/ስላሴ ዳኝነቱን
የሚተቹና ለሃሪሰን ቀይ ካርድ የግድ
መስጠት ነበረበት የሚሉ ወገኖች ደግሞ
ዳኝነቱ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ስህተቶች
እንዴት ሊቀንሱ ይገባል የሚል ጥናት
ሊሰራ ይገባል ይላሉ፡፡ የጨዋታው
መጠናቀቅ ተከትሎ ፋሲሎች ለሊቱን
ጎንደር የገቡ ሲሆን እሁድ ጠዋት የክለቡን
አሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡን ዮሴፍ
ከፈለኝ በስልክ አናግሯቸው የሚከተለውን
ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
ሃትሪክ፡- ከጨዋታው እንነሳና
እንዴት አገኘኸው?
ምንተስኖት፡- ጨዋታውን በተመለከተ
ኳሱን መሰረት ያደረገና ማጥቃት ላይ
የተመሰረተ ሰለሆነ ማራኪ እንደነበር
ነው የማውቀው፡፡ በቡድኔ አጨዋወትም
ደስተኛ ነኝ፡፡ የጨዋታ ቅመም የሚባለው
ዳኛ ነው ተገቢ ያልሆነ ውሳኔ ሲወስን
የተበደለው ክለብ ተጨዋቾች በስነልቦና
ደረጃ እየወረዱ ይመጣሉ፡፡ የሚገርምህ
እኛ እንኳን ሊበደለን ብንበደል ጭምር
አለልን ብለን አምነን የምንገባው ዳኛውን
ነው፡፡ ያመንከው ዳኛ ውሳኔ የተዛባ
ከሆነ ግን ቡድንህ ይወርዳል እኛ ላይ
የደረሰውም ይሄ ነው፡፡
ሃትሪክ፡- የደጋፊዎቹ የመቀባበል
ሂደት እንዴት አገኘኸው?
ምንተስኖት፡- ይሄ ነው ኳስ፡፡
ደጋፊው በሙሉ እንዲህ ቢቀጥል ጥሩ
ነው፤ የነበረው መንፈስ ደስ ይላል፡፡
በዘርና በሃይማኖት የተለያየውን አንድ
የሚያደርግ ቢኖር ስፖርት ነው፡፡ እግር
ኳስ ደግሞ ይህን የማድረግ አቅም አለው፡
፡ የደጋፊዎቹ አካሄድ በሌሎች ክለቦች
ደጋፊዎችም መተግበር አለበት ባይ ነኝ፡፡
ሃትሪክ፡- ወደ ዳኝነቱ እንምጣና
ተበድለናል የሚለው ሃሳብህ አሁን አለ?
ምንተስኖት፡- አዎ የልጆቹ ነጭ ደም
ፈሶም ቢሆን መበደላቸው ያሳዝናል፡፡ ዳኞች
ኮሚቴው አገር ወክለን እንደመጣን ከግምት
ከቶ የተሻለ ዳኛ ቢመድብ ደስ ይለኛል፡፡
ጨዋታው ቀመር ተሰርቶበት ነው ያልኩት
ምክንያት ስላለኝ ነው፡፡ ኢንተርናሽናል
ዳኛ ሆነህ ስትሳሳት ሆን ተብሎ ነው ወይ
ያስብልሃል ቀለል ያሉ ስህተቶች ሰዋዊ
ናቸው ውጤት የሚቀይር ስህተት ሲሆን
የቡና በረኛ መስመር አልፎ በእጁ እየነካ
ዝም የሚል ከሆነ ግን ዳኝነቱ ለአንድ ወገን
ነው ወይም ራሱ ይዞት የመጣ ተልዕኮ አለ
ለማለት እገደዳለሁ፡፡
ሃትሪክ፡- አማኑኤል ሃ/ስላሴ ተልዕኮ ይዞ
ይመጣል የሚባል አይነት ዳኛ አይደለም…
ስህተት ነው ወይስ ርግጠኛ አንተ እንዳልከው
ተልዕኮ ይዞ መጣ ማለት ይቻላል?
ምንተስኖት፡- ስም የሚያሰጥህኮ ስራህ
ነው፡፡ ጥሩ ከሰራህ የሚያስከብርህ ካልሰራህ
ደግም ተልዕኮ ይዘህ መጥተሃል ያስብልሃል፡
፡ 12 ጨዋታ ስንጫወት አንድም ቀን
ዳኞች ላይ አሳብቤ አላውቅም ችግሮችን
ውስጣዊ አድርገን ነው የሰራነው፡፡ ትክክለኛ
ያልሆነ ቀይ ካርድ በራምኬል ላይ መዝዞ
እኛ ማግኘት የነበረብንን በተለይ የሃሪሰንን
ከውጪ ኳስ በእጁ መንካት በዝምታ ማለፉ
ግን ስሜታችንን ጎድቷል፡፡
ሃትሪክ፡- ራምኬል ሎክ ይቅርታ
መጠየቁስ የዳኛውን ውሳኔ ተገቢነት
አያሳይም?
ምንተስኖት፡- በፍፁም አልጠየቀም ይሄ
የተሳሳተ መረጃ ነው ኮሚሽነሩ ሸረፋ ደሌቾ
አንተ ከመጀመሪያው ተነስተህ ነው የመታኸው
ሲለው… አብረን ስንሮጥ በእንቅስቃሴ ክንዴ
ላይ ተጋጨ ብሎ ራምኬል ሲመልስ ነው
የሰማሁት፡፡ ይሄ ለማዘናጋት ካልሆነ በቀር
ይቅርታ አልጠየቅም፡፡
ሃትሪክ፡- እርግጠኛ የሆነኮ መረጃ አለኝ…
ምንተስኖት፡- ስህተት ነው ይቅርታ
አልጠየቀም፡፡
ሃትሪክ፡- ያስያዛችሁትን ክስ
ቀጠላችሁበት?
ምንተስኖት፡- አዎ ሰው ተወክሎ ክሱን
እንዲከታተል ተደርጓል፡፡
ሃትሪክ፡- 75 በመቶ የተሸነፍነው በዳኛ
ነው በሚለው ሃሳብህ ፀንተሃል?
ምንተስኖት፡- ምክንያት አለኝኮ፡፡ ሆን
ተብሎ እንዲህ በቀይ ከወጣ ቡድኑ የተሟላ
ስለማይሆን አጨዋወቱ ይወርዳል በሚል
እሳቤ የተሰራ ይመስለኛል፡፡
ሃትሪክ፡- ፋሲል ኤሌክትሪክን 1ለ0
በረታበት ጨዋታ የመሃል ዳኛው ለአልሃሰን
ካሉሺያ የፍፁም ቅጣት ምት ከለከሉ በሚል
ኤሌክትሪኮች ክስ አስይዘዋል፡፡ ፋሲል በዚህ
ጨዋታ ተጠቅሟል የሚሉ ወገኖች አሉና
የዳኝነት ስህተቱ ሁሌም እንዳለ አያሳይም?
ምንተስኖት፡- ማሸነፍ የነበረብንን
ጨዋታ አሸንፈን ወጥተናል፡፡ በዳኝነቱ በኩል
ችግር አለ ያሉትን ኤሌክትሪኮችን ብትጠይቅ
ነው የሚሻለው፡፡ በዚህ ላይ ምንም ማለት
አልፈልግም፡፡
ቡናዎችን ስለዳኝነቱ ብትጠይቅ እንደኛ
የሚናገሩ ይመስ ልሃል?
ሃትሪክ፡- የነዳዊት እስጢፋኖስ
አለመኖር አልጎዳችሁም?
ምንተስኖት፡- ቡድኑኮ በአንድ
ግለሰብ የተወሰነ አይደለም፡፡
ሃትሪክ፡- ማለቴ ሲኒየሮች እነ
አይናለምን ጨምሮ ሲጎድሉ ጉዳቱ
አይታይም?
ምንተስኖት፡- አዎ የነአይናለም
አለመኖር ጎድቶናል፡፡ በዚህም ያለቦታቸው
እንዲጫወቱ የተደረጉም አሉ ለምሳሌ ሰይድን ያለቦታው መሃል
ላይ እንዲጫወት አድርገናል የልጆቹ አለመኖር በተ ወሰነ
መልኩ ውጤቱ ላይ ጎድቶናል፡፡
ሃትሪክ፡- ጫና ውስጥ የመሆን
ስሜት አልፈጠረብህም?
ምንተስኖት፡- የተሰጠኝን የስራ ድርሻ
በሚገባ ካልተወጣሁ ነው ጫና ውሰጥ የምገባው፡
፡ በግሌ ይሄ ስሜት አልተሰማኝም ልጆቹም
ቢሆኑ ያላቸውን አውጥተው ነው የተጠቀሙት
የክለቡ አመራሮችም ይህን ያዩ ይመስለኛል፡፡
እኔን የሚያስጨንቀኝ ሁሌም እንዲህ ያልረባ
ውሳኔ እየተሰጠ ቡድኔ እንዳይወርድ ነው
በግሌ በጫና ውስጥ አይደለሁም የስንብት
ስጋትም የለብኝም፡፡ አንድም ቀን 1 ፐርሰንት
አስጨንቆኝም አያውቅም፡፡ ለቡድኔ ከሆነ ግን
እጨነቃለሁ፡፡ ከላይ እንዲሆንም እፈልጋለሁ፡
፡ የአሰልጣኞች ስብስቡ አሪፍ ነው በርግጥ
አንዳንድ የድለላ ስራዎች አሉ እርሱም ቢሆን
አያሰጋንም፡፡ በአቅም ደረጃ ሲኒየር የተባሉ
አሰልጣኞች ውጤትን አይተናል፡፡ ሲኒየሮችን
እናከብራለን፡፡ ከነርሱም መማር እንፈልጋለን
ነገር ግን በተሰጠን ሃላፊነት በርትተን እየሰራን
ስለሆነ ምንም ስጋት የለብንም፡፡
ሃትሪክ፡- የልጆቹ ስሜት የተጎዳ
ይመስልሃል?
ምንተስኖት፡- ምንም ለውጥ አይኖርም
ስብስቡ አቅም ያለውና ምርጥ አንድነት
ያላቸው በመሆኑ ነገም ወደማሸነፍ መመለሳችን
አይቀርም፡፡ ፋሲል ባልረባ ውሳኔ ተሸንፎ
የሚፈረካከስ ቡድን አይደለም፡፡
ሃትሪክ፡- ማስተላለፍ የምትፈልገው
የመጨረሻ መልዕክት አለ?
ምንተስኖት፡- የሚመለከተው አካል ወሳኝ
ለተባሉ ጨዋታዎች ትኩረት ሰጥቶ ነፃ የሆነ
ዳኛ ሊመድብ ይገባል፡፡ ጥሩ ጥሩ ኢንተርናሽናል
ዳኞች አሉን፡፡ በርግጥ ይሄም ኢንተርናሽናል
አርቢትር ነው ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ነፃ
የሆነ ዳኝነት የሚሰጥ አርቢትር እንፈልጋለን፡
፡ በጨዋታ ተበልጠን አምነን ስንሸነፍኮ ደስ
ይላል እንቀበላለን፡፡ በተዛባ ውሳኔ አገር ላይ
ተጨዋቾች ላይ መቀለድ ግን ጥሩ አይደለም፡
፡ ሃገርና ህዝብ ወክለን መንቀሳቀሳችን መታወቅ
አለበት፡፡