ፈሲል ከተማ እግር ኳስ ክለብ ከአሰልጣኝ ምንተስኖት ጌጡና ምክትላቸውን በትናንትናው እለት መለያየቱን በያፋዊ ገጹ ያስታወቀ ሲሆን በቀጣይ ክልቡን የማን ይረከባል ለሚለው መልስ ብዙም ያላመነቱት አፄዎቹ በአሁን ሰዓት እረፍት ላይ ከሚገኙት የቀድሞ የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ መሣይ ተፊሪን በዛሬው እለት ጎንደር በመግባት በአሰልጣኝነት ቡድኑን እንደሚረከቡ ታውቋል።
አሰልጣኝ መሣይ ተፈሪ ከዚህ ቀደም ወላይታ ድቻን ለ9 ዓመታት ማሰልጠን የቻለ ሲሆን በተጨዋችነት ዘመኑ የአርባ ምንጭ ጨርቃጨርቅ የወንጂ ስኳር የኢትዮጵያ ቡና የአየር ኃይልና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጫውቶ ማሳለፉ እሚታወስ ነው፡፡