በሀዋሳ ከተማ ከ4 ዓመታት ቆይታ በሇላ ከሀይቆቹ ጋር የተለያዮው አሰልጣኝ ውበቱ አባተ መድረሻውን ፋሲል ከተማ አድርጓል፡፡
በዘንድሮው የኢትዮጵያ ኘሪሚዮር ሊግ 2 አሰልጣኞችን የቀየሩት ፋሲሎች በ2011ዓ/ም ተጠናክረው ለመቅረብ ከወዲሁ ሁነኛ ያሉትን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን በ2 አመት ኮንትራት ስምምነት ውል አስፈርዋል፡፡
ማራኪ የኳስ ፍሰት ያለው እና የኳስ ቁጥጥርን የበላይነት ለመውሰድ የሚሞክር ቡድን በመስራት የሚታወቁት አሰልጣኙ በይፋ አፄዎቹን የተረከቡ ሲሆን በቀጣይም ለሚከተሉት የአጨዋወት ዘይቤ ይሆኑኛል የሚሏቸውን የነባር ተጨዋቾችን ውል የማደስና አዳዲስ ተጨዋቾችንም ለማስፈረም ከክለቡ የስራ ሀላፊዎች ጋር ስራ መጀመራቸው ተነግሯል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ቡና፡አዳማ ከተማ ፡ሀዋሳ ከተማና በውጭ ሀገርም የሱዳኑን አልአህሊ ሸንዲ ማሰልጠናቸው ይታወቃል፡፡