የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊዎቹ ፋሲል ከነማ ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከመቐለ ጋር የተሳካ ጊዜ ያሳለፈውን ኦሰይ ማውሊን አስፈረሙ።
መቐለ 70 አንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን እንዲያነሱ ከፍተኛ ድርሻ ከነበራቸው ተጨዋቾች መካከል በቅድሚያ ሚጠቀሰው ኦሰይ ማውሊ አምና በተፈጥሮአዊ አጥቂ እጥረት የታየባቸውን አፄዎቹን ተቀላቅሏል።ከዚህ በፊት ጋብርኤል መሃመድን ከመቐለ 70 እንደርታ ያስፈረሙት ፋሲሎች ጋናዊውን አጥቂ የግላቸው ማድረግ ችለዋል።
በእስራኤል ሊግ የ6 ዓመት ቆይታ የነበረው ኦሰይ ማውሊ የፋሲል የመጀመሪያ ጨዋታውን በአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ የቀድሞ ክለቡን መቐለ 70 እንደርታን በመግጠም ሚጀምር ይሆናል።