በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትግራይ ስታድየም ላይ ደደቢትን የገጠመው ፋሲል ከነማ እምስት ግቦችን በማስቆጠር እሸነፈ።እፄዎቹ ባሳለፍነው ሳምንት ድሬዳዋን ከገጠመው ስብስብ ሁለት ቅያሬዎችን ማለትም ሰለሞን ሃብቴን በኣብዱራህማን ሙባረክ ኢዙ ኣዙካን በሽመክት ጉግሳ ሲቀይሩ ባለሜዳዎቹ ደደቢቶች በበኩላቸው በወልዋሎ ከተሸነፈው ምርጥ 11 ዳዊት ወርቁን በሃይሉ ገብረየሱስ፣መድሃንየ ብርሃነን በፋሱይኒ ኑሁ፣መድሃንየ ታደሰን በእብዱላዚዝ ዳውድ ቀይረዋል።
- ማሰታውቂያ -
የፋሲሎች የኳስ ቁጥጥር እና የግብ ሙከራ ብልጫ በታየበት የመጀመርያ እጋማሽ ሁለት ግቦችን ኣሳይቷል።ጨዋታው በተጀመረ በ3ኛው ደቂቃ ከፍፁም ቅጣት ሳጥን ግራ መስመር ጫፍ ላይ የተገኘውን ቅጣት ምት ኣምሳሉ ጥላሁን እስቆጥሮ እንግዶቹን መሪ ማድረግ ችሏል።በ3-4-3 የተጨዋቾች እደራደር ወደ ሜዳ የገቡት ደደቢቶች እጥቂያቸው ፋሱይኒ ኑሁን ኢላማ ያደረጉ ኳሶችን ቢያሻግሩም በሁለት ተከላካዮች መሃል ብቻውን የነበረው ፋሱይኒ አጋዥ ማጣቱን ተከትሎ ምንም ሊፈይድ ኣልቻለም።በኣጭር ኳሶች የደደቢትን ግብ ክልል መፈተሻቸውን የቀጠሉት ፋሲሎች 25ኛው ደቂቃ ላይ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ የተላከውን ኳስ እብዱራህማን ሙባረክ ከውስጥ ሾልኮ በማምለጥ ያገኘውን ኳስ በጥሩ ኣጨራረስ ከበረኛው እናት እሳልፎ የፋሲልን ጎል ወደ ሁለት ከፍ እድርጓል።ከሁለተኛው ግብ በኃላ በተሻለ መልኩ ወደ ፋሲል የግብ ክልል ለመድረስ የሞከሩት ደደቢቶች ፋሱይኒ ኑሁ ከቀኝ መስመር ወደ ፍፁም ቅጣት ሳጥን ሰብሮ በመግባት የሞከረውና በረጅሙ ከሚወረወሩ የእጅ ውርወራዎች እድሎችን ለመፍጠር ሞክረዋል።
በሁለተኛው እጋማሽ ደደቢቶች መድሃንየ ታደሰን በእለም ኣንተካሳ ቀይረው ሲያስገቡ እጼዎቹ ምንም የተጨዋች ቅያሬን ሳያደርጉ ጀምረዋል።ሀለተኛው እጋማሽ ከተጀመረ ከእምስት ደቂቃዎች በኃላ ሰኢድ ሃሰን ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሽመክት ጉግሳ በቀላሉ እስቆጥሮ የፋሲሎችን መሪነት ወደ 3 ልዩነት ከፍ ማድረግ ችሏል።ከሦስተኛው ግብ በኃላም ማጥቃታቸውን የቀጠሉት ፋሲሎች በ64ኛው ደቂቃ በመልሶ ማጥቃት ሙጂብ ቃሲም ይዞት የገባውን ኳስ ለኤፍሬም ኣለሙ እቀብሎት ኤፍሬም በጥሩ ሁኔታ በመጨረስ የፋሲል ኣራተኛ ግብ እስቆጥሯል።ከግቡ መቆጠር በኃላ በክብር ቱሪቡን የነበሩ ደጋፊዎች የፋሲል ኮቺንግ ስታፍና ተቀያሪ ተጨዋቾች ላይ ድንጋይ መወርወራቸው ተከትሎ ጨዋታው ከእንድ ሰዓት በላይ ሊቋረጥ ችሏል።
የፀጥታ ሃይሉ ደጋፊዎችን ከስታድየም ካወጣ በኃላ የቀሩትን 25 ደቂቃዎች እካሂዶ ፋሲሎች በሙጂብ ቃሲም እምስተኛውን ግብ ሲያስቆጥር ደደቢቶች በመድሃንየ ታደሰ እማካኝነት እስቆጥረው ጨዋታው 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ልዩነት ተጠናቋል።
ውጤቱን ተከትሎ እፄዎቹ ነጥባቸውን 43 በማድረስ ነገ ጨዋታውን ከሚያደርገው ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ 2 እጥበዋል።