የኢትዮጵያ እግር ኴስ ፌዴሬሽን በፕሪሚየር ሊጉ መላቀቅ ያሰሳፈራኛል ሲል ያለውን ስጋት ገለፀ።ከዚሁ ስጋት በመነጨ የፊታችን ዓርብና ቅዳሜ የሚካሄዱ ጨዋታዎችንም ወደ መጪው ሐሙስ እንዲተላለፍም ወሰነ።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትናንት ከሰዓት በሰጠው መግለጫ ላይ እንደገለፀው በፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ የመላቀቅ መጥፎ ጠረን እንደሚሸትና ይሄንን ችግር ለማስወገድም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ቀጣይ ጨዋታዎችን ማስተላለፍ አማራጭ የሚቀርብለት ጉዳይ ባለመሆኑ ጨዋታዎችን ማዘዋወሩን አሳውቋል።
ፌዴሬሽኑ ጨምሮ እንደገለፀው የመላለቀቅ ስጋትን ለማስወገድ በቀጣይ የሚደረጉ ጨዋታዎችን በእኩል ሰዓት ለማድረግና አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ገልፃ ቅ.ጊዮርጊስ ሀገርንና ወክሎ እንደመጫወቱ ልንረዳው ይገባልም ብለዋል በመግላጫቸው።በፕርሚየር ሊጉ አሁን ባለው ውጤት 8 ቡድኖች በወረቀት ስሌት መሰረት በመውረድ ቀጠና ውስጥ ሲሆኑ በዋናነት ዛሬ አቻ የወጣው አዲስ አበባ ከተማ፣ኢት.ንግድ ባንክ፣ድሬዳዋ ከተማ፣ጅማ አባ ቡና እና ወላይታ ዲቻ በከፍተኛ የመውረድ ስጋት ውስጥ ሆነው ውድድራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ።
ፌዴሬሽኑ በፕርሚየር ሊጉ መላቀቅ ይሸተኛል በማለት ጨዋታዎችን አስተላለፈ ፤ቅ.ጊዮርጊስ ከፋሲል ከተማ የሚያደርገው ተስተካካይ ጨዋታ ግንቦት 20 እንዲካሄድ ተወሰነ
Hat-trick Weekly Sport Newspaper Founder & Managing Editor.
The First Color Sport Newspaper in the country.