ከሀዋሳ ከተማ ጋር ላለፉት ሁለት ዓመታትን መቆየት የቻለው ፍሬው ሰለሞን /ጣቁሩ / ሀይቆቹን በመልቀቅ በአሰልጣኝ ስዩም ከበደ እሚመራው ጦሩን ተቀላቅሏል።
በዝውውር መስኮቱ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ እሚገኘው መከላከያ ተመስገን ገብረኪዳንን ከጅማ አባጅፋር፣ ዓለምነህ ግርማን ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና ብሩክ ቃልቦሬን ከወልዲያ ከተማ ለሁለት ዓመት ማስፈረሙን የመከላከያ ስፖርት ክለብ ተወካይ ኮሎኔል ንጉሴ አየለ ለሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገጽ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ክለቡ የሙሉቀን ደሳለኝ፣ ምንተስኖት ከበደ፣ ምንይሉ ወንድሙና ሽመልስ ተገኝን ኮንትራት በሁለት ዓመት ማራዘሙን አስታውቋል።