ዮውሃንስ ሳህሌን ኣሰልጣኝ ኣድርጎ የሾመው ድሬዳዋ ኣምና ከመቐለ ከተማ ጋር የተሳካ ዓመት ያሳለፈውን ፍቃዱ ደነቀን ማስፈረም ችሏል።ከኣሌክስ ተሰማ ጋር በመጣመር ጠንካራ የተከላካይ መስመር መስራት የቻለው ፍቃዱ የኣሰልጣኙን መንገድ በመከተል ወደ ትውልድ ሃገሩ ድሬ መመለስ ችሏል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ ውጤት የሆነው የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድባንክ ተጨዋች ፍቃዱ ደነቀ ሃገሩን በወጣት ቡድን መወከል ችሏል።