በክረምት ዝውውር መስኮት ዘጠኝ ተጨዋቾችን ማስፈረም የቻለው ወላይታ ድቻ መሃል ሜዳ ላይ ያለው ክፍተትን ለመሙላት የቀድሞው የሃዋሳ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ዳሽን ቢራና ደደቢት ተጨዋች በኣንድ ዓመት ውል ለጦና ንቦች ፈርሟል።ላለፋት ዓመታት በሲዳማ ቡና ጥሩ ብቃቱን ማሳየት የቻለው ፈቹል ታድዮስ ወልዴን ና በዛብህ መለዮን ያጣው የወላይታ ድቻ መሃል ክፍልን ያጠናክራል ተብሎ ይጠበቃል።
ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ወጥ ኣቋም ማሳየት የተሳነው ወላይታ ድቻ ቀጣይ ዓመት ይሄን ችግር በቋሚነት ለመፍታት በዝውውር መስኮቱ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።