The BIG INTERVIEW : SALHADIN SAIDE
ሀትሪክ፡- ረዘም ያለ ጉዳት ማስተናገድህ
ይታወቃል… እንዴት አለፍከው?
- ማሰታውቂያ -
ሳላህዲን፡- በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው
ያሳለፍኩት ወደ 8 ወር አካባቢ ጉዳት ላይ ነበርኩ
ጉዳቱም ከፍተኛ ስለነበር የተለያየ ቦታ ሄጃለሁ ትልቁ
ጉዞዬ ጀርመን የሄድኩበት ነበር፤…
ህክምናዬን በተሳካ ሁኔታ ጨርሼ ተመልሻለሁ በጉዳት ወቅት ፊዚዮና አንዳንድ ልምምዶች ስሰራ ቆይቻለው፡፡
ሀትሪክ፡- ይሄ ለዋሊያዎቹ ትልቅ
ደስታ አይመስልህም?
ሳላህዲን፡- (ሳቅ) እስቲ አብረን
እናየዋለን
ሀትሪክ፡-ከጉዳት መልስ ሊጉ ከበደህ? ወይስ?
ሳላህዲን፡- አይ የከበደኝ ነገር
የለም፡፡ ለጨዋታው ዝግጁ ለመሆንና ወቅታዊ አቋሜን ለመመለስ የተወሰኑ ጨዋታዎች ያስፈልጉኝ ነበር፡፡ ብዙ አርፌ ስለመጣሁ ወደ ጨዋታ ለመመለስ የተወሰነ ልፋት አስፈልጎኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በጉዳትህ ወቅት የነበረው
የቤተሰቦችህ ድጋፍ ምን ይመስላል?
ሳላህዲን፡- በጣም ያዘኑበት ጊዜ ነበር፡
፡ በተቃራኒው ደግሞ እንዳላዝን ከጎኔ
ሆነው ድጋፍ ሰጥተውኛልና በዚህ አጋጣሚ
ላመሰግናቸው እፈልጋለው፡፡ ቤተሰቤና
ጓደኞቼ ልጆቼንም ከጎኔ ነበሩና ምስጋናዬ
ይድረሳቸው፡፡
ሀትሪክ፡- የኛ ሀገር ተጨዋቾች ብዙ
ጊዜ ግብ የላቸውም ይባላል… ይህን እንዴት
ታየዋለህ?
ሳላህዲን፡- በርግጠኝነትማ ግብ ሊኖርህ
የግድ ይገባል ያን ለማሳካት ደግሞ ትግል
ይጠይቃል፡፡ ምን ማሳካት አለብኝ ብለህ
መነሳት ከቻልክ ነው ስኬታማ የምትሆነው፡
፡ ጊዮርጊስ ቤት ደግሞ የአፍሪካ ተሳትፎ
ለማሳካት የሊጉን ዋንጫ ለማንሣት የግድ
መነሳሳት ይኖርብሃል ይሄ ደግሞ ግዴታ
በመሆኑ ያለ ግብ መነሳት አትችልም፡፡
ሀትሪክ፡- በርካታ ተጨዋቾች የዋንጫ
ድላቸውን በቁጥር አያውቁትም… አንተስ
የዋንጫ ድልህን ታውቀዋለህ?
ሳላህዲን፡- ሀገር ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ
የዋንጫ አሸናፊ ነበርኩ፡፡ በጊዮርጊስ ማሊያ
ሙሉ ዋንጫ አግኝቻለው አምና ጉዳት ላይ
ስለነበርኩ ዋንጫው ላይ ነበርኩ ማለት ግን
ይቻላል? (ሳቅ) ከዚያ ውጪ ግን ዋንጫ
ወስጃለው፡፡ 2000 የሚድሮክ ዋንጫ፣ 2001
ፕሪሚየር ሊግና ጥሎ ማለፍ 2002 ፕሪሚየር
ሊጉን ከዚያ ከ2004 በቅጣት ከቡድኑ ጋር
አልነበርኩም ከ2005 እስከ 2008 የውጪ
ሊግ ላይ ተሳታፊ ነበርኩ 2009 መሃል ላይ
ጊዮርጊስ ገብቼ ፕሪሚየር ሊግና ጥሎ ማለፍ
ወሰድኩ 8 ፕሪሚየር ሊግና ጥሎ ማለፍ
ዋንጫ ወስጃለው ማለት እችላለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-ጊዮርጊስ ቤት ብቻ አለ ብለህ
የምትገረምበት ጉዳይ ምን ይሆን?
ሳላህዲን፡-ጊዮርጊስ ስትገባ ትልቁ ህልምህ
በአፍሪካ የክለቦች መድረክ ላይ ጥሩ ውጤት
ለማምጣትና የሊግ ዋንጫ ለማንሣት ነው…
ይሄ ጊዮርጊስ ከሌሎች ክለቦች አንፃር ያለው
ትልቁ መለያው ይመስለኛል፡፡ ቡድኑ ውስጥ
ያለው አንድነት፣ የአሸናፊነት መንፈስ
ቤተሰባዊ ትስስሩ ያስደስታል፡፡ እነኚህ ነገሮች
ሌሎች ክለቦች ውስጥ ያለ አይመስለኝም፡፡
በጊዮርጊስ ቤት ከቢ ቡድን እደግ ከሌላ ክለብ
ና ጫናው ተመሳሳይና ትልቅ ነው ከትልልቅ
ተጨዋቾች ጋር ነው የምትፋለመው…
የአዕምሮና የሰውነት አቋምን አስተካክሎ
በጥሩ አቋም ላይ ለመገኘት ጠንክሮ መስራት
ይጠበቃል፡፡ ወደ ትላልቅ የአፍሪካ ክለቦች ጋር
ሄዶ ለመጫወት ለጊዮርጊስ ተሰላፊ መሆን
ግዴታ ነው፡፡ የጊዮርጊስ ፕሮፋይል ትልቅ
መሆኑና በሌሎች አገሮች መታወቁ የዚህ
ክለብ ተጨዋቾችን ብዙ ክለቦች ይፈልጓቸዋል፡
፡ ፕሮፌሽናል ሆኖ ለመጫወት የጊዮርጊስ
ማልያ ማድረግ የግድ ነው በጊዮርጊስ ማልያ
በተሰለፍኩባቸው 6 አመታት ደስተኛ ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ሳላህዲን የወጣበት አሶሳ ከተማ
ውስጥ እንደመሆኑ እግር ኳስ በከተማው
እንዴት ይታያል?
ሳላህዲን፡- እኔ የወጣሁት ከአሶሳ ነው…
የአሶሳ ሰው ደግሞ ኳስ ይወዳል ጥሩ ጥሩ
ተጨዋቾች አሉበት አየሩ ሞቃት መሆኑ
ለተጨዋቾች ይመቻል ከዚያ የሚመጡ
ተጨዋቾች በሰውነት ግዝፈትና ጥንካሬ
ከሌሎች ቦታዎች ከሚመጡ ይለያዩ በጣም
ቢሰራበት ብዙ ሳላህዲኖች ይወጣሉ ብዬ
አስባለው፡፡
ሀትሪክ፡- ለፊዚዮቴራፒስቱ ይስሃቅ
ሽፈራው አንድ ጊዜ አንተና ጌታነህ
ሸለማችሁት አሉ… እውነት ነው?
ሳላህዲን፡- ሽልማት ብለን ባንሰቅለው ደስ
ይለኛል፡፡ ይስሃቅ የእግር ኳስ ባለውለታ ነው
ሊወደድ የሚገባ ምርጥ ሰው ነው አጠቃላይ
ተጨዋቾች የሚታከሙት እርሱ ጋር ነው፤
የሚገርምህ ደግሞ ለሚያደርገው ህክምና
ክፍያ የማይቀበል መሆኑ ነው… የተጨዋች
ቤተሰብ ቢሆንም እንኳ የነፃ አገልግሎት ነው
የሚያገኘው… ይስሀቄ ለሰብዓዊነቱ ትልቅ
ክብር ይገባዋል ከሰራው ስራ አንፃር የሚገባው
ቦታ ያልተሰጠው ቢኖር ይስሃቅ ነው… በጣም
የምወደውና የማከብረው ሰው ነው በዚህ
አጋጣሚ መናገር የምፈልገው ኳስ ከጀመርኩ
ወዲህ ጉዳት ሲያጋጥመኝ የምመላለሰው
ይስሃቅ ጋር ነው፡፡ ለኔ ምርጥ ባለሙያ ነው
ረጅም እድሜ እመኝለታለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ቀላል ነው የምትለው ጨዋታ
ይኖር ይሆን?
ሳላህዲን፡- ብዙ ቡድኖች ከኛ ጋር
ሲጫወቱ ወጥረው ነው የሚፋለሙት ሁሉም
ተጨዋቾች መታየት ስለሚፈልጉ ያላቸውን
ነው አውጥተው የሚጫወቱት ሁሉም ቡድን
ለኛ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ ነው የሚገባው፡
፡ ሁሉም ቡድኖች ከጊዮርጊስ ጋር ሲጫወቱ
ያላቸውን ለማሳየት ስለሚገቡ ለእኛ ቀላል
የሚባል ጨዋታ የለም በግሌ ግን ለትንሽም
ይሁን ትልቅ ቡድን ክብር አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- ከተቃራኒ ክለቦች መሀል
አስቸጋሪ ነው የምትለው ተከላካይ አለ?
ሳላህዲን፡- በዚህ ደረጃ ለይቼ የምጠራው
ያለ አይመስለኝም ነገር ግን ሁሉም
በተመሳሳይ ደረጃ አስቸጋሪ ናቸው፡፡ ከጊዮርጊስ
ጋር ከመጫወቱ በፊት እንደነበረው ወረደ ያለ
አቋም ሣይሆን ያላቸውን ይዘው ስለሚመጡ
ሁሉም ያስቸግራሉ… ነገር ግን ከአቅም አንፃር
ሳይሆን ከባህሪ አንፃር ስናየው የሚተናኮሉ
ተጨዋቾች ደስ አይሉኝም ወዳልሆነ ስሜት
ውስጥ ለማስገባት የሚያነሳሱ ተጨዋቾች
አሉ ይሄ ልክ አይደለም ድርጊቱን በጣም
ነው የምጠላው… ኳስ በሌለበት መሳደብና
መማታት የሚወዱ አሉ… ይሄ የብዙዎቹ
ባህሪ ነው ያተግባር ደስ አይለኝም በዚህ ባህሪ
አስቸጋሪ የሚባሉ አሉ…እነዚህ ሰዎች ከዚህ
ድርጊታቸው ቢታቀቡ ደስ ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡-እምነትህ በኳሱ ላይ ላለህ
ዲስፕሊንና ታታሪነት ጨመረልኝ የምትለው
ነገር አለ?
ሳላህዲን፡- በርግጥም እምነቴን አከብራ
ለው የምችለው የሚጠበቅብኝን ለማድረግ
እጥራለሁ፡፡ እምነትና ኳስ ይለያያል ኳስን
በጣም እወዳለሁ እምነቴን ደግሞ አከብራለው
በእርግጥም ለስኬቴም እምነቴ ትልቅ ድጋፍ
አድርጓል ትልቅ ተጨዋች ለመሆን ሙያውን
ማክበር ታማኝ መሆንና ከስፖርቱ ጋር
የማይሄድውን ለይቶ ማወቅ የግድ ነው…
አንድ ተጨዋች ኳሱ የማይወደውን በመተው
ተጨማሪ ልምምድ በመስራትና አመጋገቡንበማስተካከል ወዳለመበት ግብ መጓዝ ይችላል፤
ስፖርቱ የሚፈልገውን አድርጎ የማይፈልገውን
ደግሞ መተው ማለት ስፖርቱን ማክበር
ማለት ነው… ይሄን ለማድረጌ ደግሞ እምነቴ
ትልቅ እገዛ አድርጓል፡፡
ሀትሪክ፡- ጎበዝ አጥቂ ነኝ ለማለት
ትደፍራለህ…?
ሳላህዲን፡- (ሳቅ) ምንጊዜም ጥሩ አጥቂ
ለመሆን እጥራለው ከዚያ ውጪ ያለውን
ለተመልካቹ የምተወው ይሆናል (ሳቅ)
ሀትሪክ፡- ወደ ሜዳ ስትገባ ዋነኛ ግብህ
ማሸነፍ ብቻ ነው? ወይስ አቻና መሸነፍ
እንዳለ አስበህ ነው የምትገባው?
ሳላህዲን፡- ምንጊዜም የትም ክለብ
ልሁን የትኛውም ቦታ ላይ ልጫወት
መሸነፍን በጣም እጠላለው አቻም እንኳን
ብዙ አይመቸኝም በግጥሚያ ተሸንፌ ወደ
ነበርኩበት ሙድ ለመመለስ ከ2 ሳምንት
በላይ ይፈጅብኛል፡፡ ቀጣዩ ጌም ላይ በእልህ
ተነሳስቼ ማሸነፍ አለብኝ ያኔ ነው ሽንፈቴን
የምረሳው… አለበለዚያ ወደነበርኩበት
ለመመለስ እቸገራለው ሜዳ ስገባ ዋና ዓላማና
ልቤ ውስጥ ያለው ማሸነፍ ብቻ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ያለህበት ክለብ ጊዮርጊስ መሆኑ
ለዚህ ያልሸነፍ ስሜት አበቃኝ ትላለህ?
ወይስ?
ሳላህዲን፡- ሙገርም እያለሁ ያለኝ
ባህሪ ይሄ ነው ከልጅነቴ ጀምሮ ያለኝ ባህሪ
ነው ልምምድ ላይ ስንሸነፍም እንደ ዋናው
ግጥሚያም ባይሆን እናደዳለሁ፡፡ በቃ
መሸነፍን ጠልቼ ኖሬያለሁ ማለት ይቻላል፡፡
ሀትሪክ፡- ለውጪና የሀገር ውስጥ
አሰልጣኞች ያለህ ስሜት ምን ይመስላል?
ሳላህዲን፡- ብዙ አሰልጣኝ የራሱ
ፍልስፍና ይኖረዋል ለአሰልጣኙ ክብር
ሰጥተህ የሚሰጠውን ልምምድ በትጋት ሠርቶ
ተግባራዊ ማድረግ ከኛ ይጠበቃል፡፡ ሜዳ ላይ
ያለህን አውጥተህ ካሳየህ ለሚመጣው ውጤት
ኃላፊነቱ የአሰልጣኙ ይሆናል ለሀገር ውስጥም
ይሁን ለውጪ አሰልጣኞች ተመሳሳይ ክብር
አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡-የአሰልጣኝ ዋነኛ ችሎታ
የምትለው የትኛው ነው?
ሳላህዲን፡- ስልጠናኮ በአሁኑ ወቅት
ድብቅ ነገር የለውም… የነ ማን.ሲቲ የስልጠና
ሂደትና የዘመናዊነት የስልጠና መንገድን
ከኢንተርኔት አውርዶ ማየት ይቻላል፡፡ ዋናው
እኔ የምሰጠውን ስልጠና ተቀብሎ ተጨዋቹ
ሜዳ ላይ ይተገብራል ወይ? ካልተገበረ ከእኔ
ወይም ከርሱ የጎደለው ምንድነው የሚለውን
መመለስ የአሠልጣኙን አቅም ይጠይቃል፡
፡ አሰልጣኙ ከጨዋታ በፊት ተጨዋቾቹን
የሚያነሳሳበት መልበሻ ክፍሉን የሚመራበት
መንገድ የአሰልጣኙን አቅም ይፈትናል፡፡
ትልቁ ነገር ይሄ ነው፡፡
ሀትሪክ፡-ከጉዳት መልስ ስትመለስ
የተገረምክበት ጉዳይ አለ?
ሳላህዲን፡-በጉዳት ወቅት ኳሱን የማይበት
ጊዜ አልነበረኝም ፊዚዮና ጂም እጠቀም
ስለነበር እዚያ ላይ ትኩረት አድርጌ ቆይቻለሁ፡
፡ ትንሽ የገረመኝ አምና የኛ ቡድን ጥሩ
አልነበረም፡፡ የጨረስንበት ነጥብ ከሌላው ጊዜ
ዝቅ ያለ ነበርና እንዴት ሆነ ብዬ ሳስብና
ስገረም ነበር… አሁን ወደ ጨዋታ በመመለሴ
አምና ካቻምናና ዘንድር ያለውን ማነፃፀር
እችላለሁ ብዬ አስባለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከተጨዋቾች ከሚገኘው ችሎታ
ይልቅ ለነሱ የሚከፈለው ደመወዝ ይበልጣል
የሚሉ አሉ አንተስ ምን ትላለህ?
ሳላህዲን፡- ይሄኮ ሙያ አይጠይቅም ጥሩ
አቋም አሳይቶ ወደ ክለቡ ሲዛወር ወቅታዊ
አቅሙ ጥሩ ላይሆን ይችላል ያ አይችልም
ማለት አይደለም አመቱ ሲገመገም ነው ጥሩ
ነው አይደለም የሚባለው… ወደ ዝውውሩ
ስንገባ ተጨዋቹም የፈረመው ክለቡም
ያስፈረመው በግድ ሳይሆን በስምምነት
ይመስለኛል፡፡ የክፍያው ስርዓትም በዚህ
መንገድ ነው መታየት ያለበት እንጂ ክፍያው
በዛ አነሰ የሚለው ብዙም ምቾት አይሰጠኝም፡፡
ሀትሪክ፡- ከኳስ ውጪ በምንድነው ዘና
የምትለው?
ሳላህዲን፡- ቤተሰብ አለኝ ባለትዳርና
የ3 ልጆች አባት ነኝ ከቤተሰቤ ጋር ነው
የማሳልፈው ፊልምና ቲያትር ብዙም
አይመቸኝም፡፡ የ2 ሳምንት እረፍት ሳገኝ ሃዋሳ
ባህርዳር መሄድ ያዝናናኛል አንዳንዴም ወደ
ውጪ ሀገር ሄጄ ከጓደኞቼ ጋር እዝናናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- እስቲ ቤተሰቦችህን አስተዋ
ውቀን?
ሳላህዲን፡- ባለቤቴ ወ/ሮ ሳሚራ
መሀመድ ትባላለች በጉዳቴ ወቅት ትልቁን
ቦታ የምትወስደው እርሷናት፡፡ ከጎኔ ሆና
ስታበረታታኝ ነበር ከ5 ወር በፊት 3ኛውን
ልጃችንን ወልዳለች… ሁሉም ወንዶችና
ናቸው…. የ5፣ የ3 እና የ5 ወር ልጆች አባት
ነኝ… ይህ ቤተሰብ በህይወቴ ውስጥ ትልቁን
ስፍራ ይይዛል በጣም እወዳቸዋለው (ሳቅ)
ሀትሪክ፡-ትዳር በመመስረትህ ጠቀመኝ
የምትለው አለ?
ሳላህዲን፡-ትዳር መመስረቴና ልጆች
መውለዴ ራሱን የቻለ ደስታ አለው…
ከዚያም በተጨማሪ ለሙያዬ ቦታ እንድሰጥ
ልምምዴን አጠናክሬ እንድሰራ አመጋገቤን
እንዳስተካክል በማድረጉ በኩል ቤተሰቤ ትልቅ
ድርሻ አለው… ባለቤቴ ከልምምድ በፊትና
በኋላ አመጋገቤን ተረድታ በማስተካከል ትልቅ
ድጋፍ እያደረገችልኝ ነው በዚህ አጋጣሚ
ስለሁሉም ላመሰግናት እፈልጋለው፡፡ ልጆቼም
የመኖር ፍላጎቴን ከፍ አድርገውታል…
በአጠቃላይ በመሰረትኩት ቤተሰብ ደስተኛ
ነኝ፡፡
ሀትሪክ፡- የእግር ኳሳችንን የዳኝነት
ሂደት እንዴት ታየዋለህ?
ሳላህዲን፡- ዳኝነት ያስቸግራል…
ደጋፊው ስሜታዊ መሆኑ ደግሞ አንዳንዴ
ነገሮችን ወዳልሆነ አቅጣጫ ይወስዳል፡፡ አንድ
አባባል አለ… “በወንድ ልጅ ፀብ መሃል ቂም
የለም” ይባላል አንዳንዴ በስሜት ተነሳስተህ
ላለመሸነፍ ካለህ አቋም አንፃር ግጭት ሊከሰት
ይችላል ያ ግጭት ባይከሰት ጥሩ ነው ቢከሰት
ግን ዘላቂ መሆን የለበትም፡፡ ጨዋታው
ሲያበቃ ፀቡም መቆም አለበት
ብዬ አስባለው ተጨዋቾችም ሆነ ደጋፊውም ስሜታዊ መሆን የለባቸውም በተጨዋች መሀል
የሚነሣው ፀብም ደጋፊን ሊያነሳሳ የዳኛውን ውሳኔ
ሊያዛባ ይችላልና እዚህ ላይ ጥንቃቄ መድረግ አለበት ባይ ነኝ፡፡ ዳኝነቱ ብዙም የሚከፋ አይደለም፡፡
ሀትሪክ ፡ – ሳላሀዲን ፊት ለፊት ይናገራል …
ወይስ ስሜቱን ይደብቃል?
ሳላህዲን፡ – ሃምሳ ሀምሳነው፡፡ ባላንስ
የ ማ ደ ር ግ ይመለኛል…
የ ሰ ው ስሜትን ላለመንካት
የምጠነቀቀውን ያህል ፊት ለፊት የምናገር
ሰው ነኝ እውነትን እውነት ነው ብሎ ፊት ለፊት በመናገርም አምናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ዋሊያዎቹን ዘንድሮ
እቀላቀላለሁ ብለህ ትገምታለህ?
ሳላህዲን፡- (ሳቅ) ምንጊዜም ዋናው
የአሰልጣኙ ፍላጎት ነው በስም ሳይሆን በሜዳ
ላይ አቋም የሚታይ ስለሆነ ከኔ አቋሜን
አስተካክዬ ተፈላጊ ተጨዋች መሆኔን ማሳየት
ይጠበቅብኛል፡፡ እግር ኳስ መጫወት እስካቆም
ድረስ ግን ለሙያዬ መክፈል ያለብኝ ዋጋ
እከፍላለው፡፡
ሀትሪክ፡- የ2011 የቅዱስ ጊዮርጊስ እቅድ
ምንድነው?
ሳላህዲን፡- ትልቁ እቅዳችን የፕሪሚየር
ሊጉን ዋንጫ ማንሳት*ነው… ከጓደኞቼ ጋር
ሆንን ክለባችንን*ለዋንጫ አብቅተን
ወደ አፍሪካ መድረክ መመለስ ነው
ዋናው የቤት ስራችን፡፡
ሀትሪክ ፡- ወቅታዊ የቅዱስ ጊዮርጊስ አቋም ግን ደስ
የማይል ነው?
ሳላህዲን፡- አዎ… ጊዮርጊስ
ቤት ብዙ ጊዜ ጅማሬ ላይ ድክመት
የተለመደ እየሆነ ነው…በሂደት
ድክመታችንን እየቀረፍን የምንሄድበት
መንገድ በየአመቱ እየታየ ነው… ይሄ
መስተካከል አለበት ለዘንድሮው ገና ብዙ
ጨዋታዎች ይቀራሉ፡፡ ከፊት ለፊታችን
ያለውን ጨዋታ እያሸነፍን መጓዝ ነው
የሚጠበቅብን በቀጣይ ጨዋታዎች
ድክመታችንን የምናስወግድ ይሆናል፡፡
ሀትሪክ፡ የፕሪሚየር ሊጉ የፉክክር
መንፈስ ተቀራራቢ አልሆነም-?
ሳላህዲን፡- አይ አይ ለኛ ሲሆን ይለያል…
ሁሉም ክለቦች ለጊዮርጊስ አስቸጋሪ ናቸው፡
፡ ተጨዋቾቹም መታየት ስለሚፈልጉ ከእኛ
ጋር ሲጫወቱ ያስቸግሩናል፡፡ በእርግጥ የሊጉ
የፉክክር መንፈስም ጠንከር ብሎብኛል፡፡ ነገር
ግን ሁሉም ከኛ ጋር ሲጫወቱ አስቸጋሪ
የመሆናቸው ጉዳይ አሁንም ቀጥሏል፡፡
ሀትሪክ፡- ሳላህዲንን የቀየረ አሰልጣኝ
ማን ነው ብትባል መናገር ይቻላል?
ሳላህዲን፡- ለ4 አመት (ከ15፣ ከ13 ከ17
አመት በታች) ፕሮጀክት ሰልጥኜያለሁ ያኔ
አሰልጣኜ የነበረው ጋሻው መኮንን ትልቁን
ድርሻ ይወስዳል፡፡ ወደ ሙገር ያመጡኝ
አሰልጣኝ አዳነ ገ/የሱስ እሣቸውም ከቢ
እንዳደኩ ነው ዋናው ቡድን ገብቼ እንድሰለፍ
ያደረጉኝ ለሁለቱም ትልቅ ክብር አለኝ
በነገራችን ላይ በሙገር የመጀመሪያ አመት
ቆይታዬ ከ12 ጎል በላይ አስቆጥሬያለው፡፡
ሀትሪክ፡- የምታመሰግነው ሰው ካለ
እድሉን ልስጥህ?
ሳላህዲን፡- ከጉዳት አገግሜ ተመልሻለው
ለዚህ ደግሞ አላህን አመሰግናለሁ፡፡ ከዚያ
ቤተሰቦቼ ባለቤቴ፣ እናት ወንድም እህቶቼ
ጓደኞቼን ከጎኔ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዬ የላቀ
ነው ደጋፊዎቻችን ደግሞ ቡድኑ ጥሩ
ይሁን አይሁን ከጎናችን ሊሆኑ ይገባል፡፡
እንደ 12ኛ ተጨዋች ሙሉ ድጋፋቸው ሊለየን አይገባም ዋናውግባችን ሻምፒዮን ሆነን ወደ አፍሪካ
ክለቦች ፉክክር መመለስ በመሆኑ ድጋፋቸውን በደንብ እንፈልጋለን ከጎናችን እንደሚሆኑም
ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እስካሁን
ለነበረውድጋፋቸውም ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ፎቶ ምንጭ © – ሀትሪክ አርካይቭ
-መኮንን አየለ ኢንተርናሽናል ፎቶግራፈር
-googel