በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች መካከል መከላከያን ያስተናገዱት ወልዋሎ አዲግራት ከ1ዓመት በኃላ በሜዳቸው የ1-0 ሽንፈትን በመከላከያ አስተናግደዋል፡፡
በጨዋታው መጀመርያ ወልዋሎዎች 4-3-3 አሰላለፍ ይዘው የገቡ ሲሆኑ በአንፃሩ በመከላከያዎች 4-5-1 አሰላለፍ ይዘው ወደ ሜዳ ገብተዋል ከመጀመርያው 45 የመጀመርያ የጨዋታ ክፍለ ግዜ መከላከል መርጠው የተጫወቱ መከላከያዎቹ ሲሆኑ ወልዋሎዋች በአንፃሩ በኳስ ቁጥጥር ብልጫው ነበራቸው፡፡
በ 33ኛ ደቂቃ ላይ አማኑኤል ተሾመ በቀኝ መስመር የላካትን ኳስ የወልዋሎው ግብ ጠባቂ ዘውዱ መስፍን እና ተከላካዮ በረከት የፈጠሩት ያለመግባባት ተጠቅሞ ምንይሉ ወንድሙ አስቆጥሮ ጦሩን ቀዳሚ አድርጎ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡
ከእረፍት መልስ ከነጉዳቱ ተሰልፎ የነበረው አፍወርቅ ሃይሉ አስወጥተው ብሩክ አየለ ቀይረው ጨዋታውን የጀመሩት ወልዋሎዎች የተደራጀውን የመከላከያዎች የተከላካይ መስመርና ጥሩ የነበረው በረኛቸው አቤል ማሞ መስመር ሰብረው ማለፍ ሳይችሉ ሊሸነፍ ተገደዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በእለቱ በወልዋሎዎች ጥሩ የነበረው እንየው ካሳሁንና የመከላከያው ሳሚኤል ሳሊሶ እርስ በርስ በመጣለት የተጋጩ ሲሆን ሁለቱም በቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግደዋል፡፡
በሁለቱም በኩል 6ቢጫ የካርድች ተመዘዋል፡፡
ባጠቃላይ በሁለቱም 45ደቂቃዎች በመከላከሉም በመሃል ክፍሉም መከላከያዎች የተሻሉና የመናበብ ጥሩ የስነልቦና ቅንጅት የነበራቸው ሲሆኑ ባንፃሩ ለመከላከያ አጨዋወት በሚመች መልኩ ረጅም ኳስ ሲጫወቱ የነበሩት ወልዋሎዎች ከወትሮው ወርደው ታይተዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ብርሃነ ገብረእግዚአብሔር -ወልዋሎ አዲግራት
“እነሱ አሸንፈውናል በራሳችን ስህተት በፈጠርነው አጋጣሚ ተጠቅመዋል፡፡ እንጂ በኳስ ቁጥጥር እኛ የተሻልን ነበርን፡፡ ቀድመው ግብ ስላስቆጠሩብን ስሜታዊ ሆነን በመግባታችን ተረጋግተን መጫወት አልቻልንም፡፡ በዚህም ልንሸነፍ ተገደናል በመሃል ክፍልም ተበልጠን ነበር::”
ሻምበል ምንያምር ፀጋየ-መከላከያ
ከወልዋሎ ያገኘነው እንደ 3ነጥብ ሳይሆን እንደ 6ነጥብ ነው እምናየው ወልዋሎ አዲስ ክለብ አይመስልም ፡፡ ወደዚህ የመጣነው ሁለት አላማ ይዘን ነበር ከቻልን ማሸነፍ ካልቻልን አቻ ለመውጣት ነበር ፡፡የመጀመርያው እቅዳችን አሳክተናል ስለ ደጋፊው ቃላት ያጥረኛል ደጋፊው ገና ከመግባታችን ጥሩ አቀባበል አድርጎልናል በሜዳም በሚገባና በስርአት ኳስ ለተጫወተ ይደግፋል ቡና ስንጠጣ እንኳን ማን እንደሚከፍለው አናቀውም ነበር እናመሰግናለን”