ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ጥር 01/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጅማ አባጅፋር ላይ ሁለት አስደናቂ ግቦችን ያስቆጠረው የቅዱስ ጊዮርጊሱ አበባው ቡታቆ በተለይ ከሀትሪክ ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡ መከላከያ ከ ፋሰል ከተማ ባደረጉት ጨዋታ ድንቅ አቋሙን ማሳየት የቻለው ዳዊት እሰጢፋኖስ ስለ አፄዎቹ አቋምና ስለራሱ ወቅታዊ ብቃት ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ጣፋጭ ቆይታን አድርጓል።
ከባህር ማዶ፡- ከባለፈው የዝውውር መስኮት ጀምሮ ከሊቨርፑል ጋር ሊያይ ጫፍ ደርሶ የነበረው ፊሊፕ ኮቲንሆ ባርሳን መቀላቀሉን ተከትሎ ከህልሙ ጋር ስለመገናኘቱ ፤ በሰፊው ተዳሷል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በኦልዲስ በት ጉዲስ አምዳችን ደግሞ “ህይወት እንደፈለኳት ልትሆንልኝ ባትችልምየሰዎች ምክርና የቅርብ ድጋፍ ግን ተስፋ እንዳልቆርጥ አድርጓኛ፡፡ ከሚለው የቀድሞ ተጫዋች ንጋቱ ታደሰ ጋር ቆይታ አድርገናል።
እናም ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ