አርባምንጭ ከተማ እና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማሪያም የመለያየታቸው ነገር እርግጥ ሆኗል፡፡
አሰልጣኙ ከክለቡ እንዲሰናበቱ እንደ ምክኒያት የቀረበው በ2010 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ባስመዘገቡት ውጤት ሲሆን በ8ጨዋታዎች 4ተሸነፈው 3አቻ በመውጣት አንድ ጨዋታ ብቻ ያሸነፉ ሲሆን በ6ነጥብ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ 14ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጡ በመቻላቸው ነው፡፡ አሰልጣኙ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከውጪ እና ከሀገር ውስጥ 6 ተጫዋቾችን ቢያስፈርሙም ያስመዘገቡት ውጤት የክለቡን የቦርድ አካላትና የቡድኑን ደጋፊዎች ያላስደሰተ መሆኑ እንደምክኒያት ተጠቅሷል፡፡
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም ስለ ጉዳዮ ከድህረ ገፃችን ጋር ባደረጉት ቆይታ
ክለቡ ለተጫዋቾች እና ለአሰልጣኞች ደሞዝ ፤ ትጥቅ ፤ እና የምግብ አገለግሎት በተገቢ ሆኔታ ሊያቀርብ አልቻለም ፡፡ ያለበትን ጉድለቶች እንዲያሟላ በተደጋጋሚ ስጠይቅ ቆይቻለሁ፡፡ ቦርዱ ይህን ሳያሟላ ወጤት መፈለጉ እያስገረመኝ ነው፡፡
ከቡድኑ ጋር ብለያይም አዲስ ነገር አይደለም የትም ሄጄ ማሰልጠን እችላለሁ በአጭር ቀናት ውስጥ አዲስ ክለብ እንደምይዝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ነገ ወደ አዲስአበባ እመለሳለሁ ፡፡ ክለቡ ላደረገልኝ ነገር አመሰግናለሁ ፡፡አሁን የተፈጠረው ነገር ለኔ ትምህርት ሆኖኛል፡፡ “በማለት ለድህረገፃችን አስተያየታቸውን አጠቃለዋል
የአርባምንጭ ከተማ ኘሬዚዳንት አቶ ፀጋዬ ጊሌ በበኩላቸው “አሰልጣኙ እንደሚጠቅመን እናውቃለን ነገር ውጤት እና ውጤትን ተንተርሰን፡አሰልጣኙን ልናሰናብት ተገደናል፡፡ በሄደበት ሁሉ መልካሙን እንመኝለታለን” በማለት አስተያየታቸውን ለድህረ-ገጻችን ተናግረዋል ፡፡
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማሪያም ከዚህ በፊት ትራንስ ኢትዮጵያን ፤ ሀረር ከተማን ፤ኢትዮጵያ ቡናን ፤ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ፤ ማሰልጠናቸው እሚታወስ ነው