ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ አንጋፋውን አሰልጣኝ ብርሀኔ ገ/እግዚአብሔርን አሰናበት
በ2009 ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ወድድርን የበላይ በመሆን በ2010 ዓ.ም ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲን ወደ ኘሪሜየር ሊጉ ማስገባት የቻሉት አሰልጣኝ ብርሀኔ ገብረእግዚአብሔር በቅርብ ሳምንታት ክለቡ በተከታታይ በጣለው ነጥብ የመነሳታቸው ምክኒያት መሆኑን ተሰምቷል ፡፡
የክለቡ ቦርድ ትናንት ማታ ባካሄደው እረጅም ሰዓት ከፈጅ ስብሰባ በኃላ አሰልጣኙ ማሰናበቱን ሀትሪክ ድህረ ገፅ ከውስጥ ምንጮች ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
ወልዋሎ አዲግራት ዮንቨርሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ በ12ጨዋታዎች 2አሸንፎ፤ በ7አቻ ፤በ3ጨዋታዎች ተሸንፎ በ13 ነጥብ በ10ኛ ደረጃ ላይ ሊቀመጥ ችሏል
- ማሰታውቂያ -
በቀጣይ ከአሰልጣኙ ጋር ለሚነሱ ጥያቄዎች አሰልጣኝ ብርሀኔ ገብረእግዚአብሔር የሰጡትን አሰተያየት ይዘን እንቀርባለን፡፡