በካፍ ቻምፒየንሰ ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኮንጎው ኤ ኤስ ሊዮፓርድስ ይጫወታል
ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ከኮንጎው ኤ ኤስ ሊዮፓርድስ ጋር የፊታችን እሁድ በካፍ ቻምፒየንሰ ሊግ የመጀመርያ ዙር ጥሎ ማለፍ ጨዋታውን ያደርጋል።
በ2017ቱ የቶታል አፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የሲሸልሱን ኮቲዲኦር ደርሶ መልስ በመርታት ወደ ጥሎ ማለፍ የገባው ቅዱስ ጊዮርጊስ፥ ከኮንጎውን ተወካይ ሊዮፓርድስን ጋር እሁድ በዶሊሴ ከተማ ይጫወታል።
- ማሰታውቂያ -
ወደ ስፍራው ያቀኑ 18 ተጫዋቾችን አሰልጣኝ ማርት ኖይ ይፋ ያደረጉ ሲሆን፥ በሲሸልሱ ጉዞ ላይ የነበሩት ፍሬው ጌታሁን፣ ብሩኖ ኮኔ እና አንዳርጋቸው ይላቅ ተቀንሰዋል።በእነዚህ ተጫዋቾች ምትክም ዘሪሁን ታደለ፣ ፍሬዘር ካሳ እና ያስር ሙጌርዋ ተካተዋል።
በሌላ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የግብጹ አልሀሊ ከደቡብ አፍሪካው ቢድቬስት፣ የታንዛንያው ያንግ አፍሪካስ ከዜናኮ ነገ ከምሽቱ 1 ስአት ከ30 ላይ ይጫወታሉ።
ኤ ኤስ ሊዮፓርድስ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ሪቨር ዩናይትድ ከኤልሜሪክ፣ ዛማሌክ ከኢንጉ ሬንጀርስ እሁድ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
ወደ ኮንጎ የተጓዘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ልኡካን ቡድን አባላት ዝርዝር
1. አቶ ታፈሰ በቀለ — የቡድን መሪ
2. አቶ ኤፍሬም ግዛቸው — የቴክኒክ አማካሪ
3. ሚ/ር ማርቲን ኖይ — ዋና አሰልጣኝ
4. ፋሲል ተካልኝ — ም/አሰልጣኝ
5. ዘሪሁን ሸንገታ — ም/አሰልጣኝ
6. እንዴዚ ኤሚ — የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ
7. ዘላለም አዱኛ — ወጌሻ
ተጨዋቾች
1. ሮበርት ኦዶንግካራ
2. ዘሪሁን ታደለ
3. ደጉ ደበበ
4. አበባው ቡጣቆ
5. ሳልሃዲን በርጌቾ
6. አስቻለው ታመነ
7. መሃሪ መና
8. ፍሬዘር ካሳ
9. ምንተስኖት አዳነ
10. ናትናኤል ዘለቀ
11. ተስፋዬ አለባቸው
12. አብዱልከሪም ዞኮ
13. ያስር ሙጌርዋ
14. በሃይሉ አሰፋ
15. አቡበከር ሳኒ
16. ፕሪንስ ሰቨሪን
17. ሳልሃዲን ሰዒድ
18. አዳነ ግርማ