በ1ኛ ሳምንት መደረግ የነበረበት የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ጨዎታ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና 1-1 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
ልክ 11:31 ሲል የጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በደጋፊ ድባብ የታጀበ ነበር፡፡
በ4ኛ ደቂቃ ላይ ከመሀል ሜዳ ለሳሙኤል ሳኑሚ የጣለለት ኳስ ከጨዋታ ውጪ ሆኗል፡፡ ከ4 ደቂቃ በኃላ አዲስ ግደይ በግል ጥረቱ እየገፋ ይዞ የገባውን ኳስ አክርሮ ሲመታ ሀሪስተን ሄሱ ሊያወጣት ችሏል፡፡
በእለቱ በጨዋታው ደንቅ ከነበሩት የኢት.ቡናው አስራት ቱንጆ ከ ቀኝ መስመር እየተነሳ ወደ ግብ ክልል እሚጥላቸው ኳሶች እንዲሁም ከሳምሶን ጥላሁን እና መስዑድ መሀመድ ጋር የነበረው ጥምረት የሲዳማ ተከላካዮች ስራ እንዲበዛባቸው ማድረግን ችሏል፡፡የመጀመሪያው አጋማሽ ያለግብ ሲጠናቀቅ ከእረፍት መልስ በ52’ደቂቃ አዲስ ግደይ በግል ጥረቱ ያገኛትን ኳስ ቶማስ ስምረቱን እና ሀሪስተን ሄሱን በማለፈ የመጀመሪያ ጎል በማስቆጠር 1-0 ቡድኑን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡ ከጎልዋ መቆጠር በኃላ ሳሙኤል ሳኑሚ ያገኛትን ኳስ ከሲዳማ ቡና በረኛ ጋር አንድ ለ አንድ ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በ68’ኛ ደቂቃ ላይ የሲዳማ ተከላካዮች በግብ ክልልቸው ውስጥ በእጅ በመንካታቸው የተሰጠችውን ፍፅም ቅጣት ምት ኤሊያስ ማሞ በማስቆጠር ኢትዮጵያ ቡናን አቻ ማድረግ ችሏል፡፡
ከግቧ መቆጠር በኃላ ሲዳማ ቡናዎች አንድ ነጥብ ይዘው ለመውጣት በተለያዩ ምክኒያቶች ሰዓት ሲያባክኑ ተስተውሏል፡፡
አልፎ አልፎ በመልሶ ማጥቃት አጨዋወት ወደ ጎል እሚደርሰው የአለማየሁ አባይነህ ቡድን ሲዳማ ቡና በ73’ደቂቃ ላይ የቡና ተከላካዮች የሰሩትን ስህተት ተጠቅሞ ያገኛት ኳስ ተጨርፋ ወጣልች ይህም ለሲዳማ ቡናዎች እምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች፡፡
ከ4ደቂቃዎች በኃላ ሳምሶን ጥላሁን በግሩም ሁኔታ በመሰንጠቅ ያሳለፈለትን ኳስ በረከት ይስሀቅ ቺፕ በማድረግ አስቆጥራለሁ ሲል የሲዳማ ቡና በረኛ መሣይ አያኖ ተጨርፎ ሊወጣ ችሏል፡፡
ከረፍት መልስ የሲዳማ ቡና ተከላካይ ክፍል ተጫዋቾች ስራ በዝቶባቸው ተስተውሏል፡፡
በ89′ ደቂቃ የሲዳማ ቡናው አማካይ ተከላካይ ትርታይ ደመቀ በአስናቀ ሞገስ ላይ በሰራው ጥፋት በመጀመሪያ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ የጨዋታው ክፍለ ግዜ 90 ደቂቃ መጠናቀቁን ተከትሎ 5 የባከኑ ደቂቃዎችን 4ኛ ዳኛ ሲያሳዮ ከደጋፊዎች እና ከኢትዮጵያ ቡና አስልጣኞች ተቃውሞ ሲያሰሙ ተስተውሏል፡፡ በዚሁ ጨዋታው 1-1 በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
ኮስታዲን ፓፒች ኢትዮጵያ ቡና
-ካለፈው ጨዋታ ዛሬ በተሻለ ተጫውተናል በጣይ ከዚህ በተሻለ ሆነን እንቀርባለን፡፡
-ተጋጣሚያችን በታክቲክ የሚጫወት ጠንካራ ቡድን ነው አንድ ነጥብ ይዘው በመመለሳቸው እንኳን ደስ አላቹሁ ለማለት እፈልጋለሁ፡፡
አለማየሁ አባይነህ ሲዳማ ቡና
-ዛሬ ሜዳ ላይ ይዘነው የገባነው ታክቲክ ላይ ነው ትኩረት አድርገን የገባነው
-ቡና በደጋፊ እሚታወቅ ነው ዛሬ ቡድኑ ሳይሆን ደጋፊው ነው የተጫወተው፡፡
– በደጋፊ እሚንቀሳቀስ ቡድን ነው ኢት.ቡና ሰዓት ማባከን እንደ እስትራቴጂ አልመለከተውም፡ ሆኖም ተሳክቶልኝ አንድ ነጥብ ይዘን መመለስ ችለናል፡፡