የኦሮሚያ ሲቲ ካፕ የሶስተኛ ቀን ሁለት ጨዋታዎች የተከናወኑ ሲሆን ሰበታ ከተማ እና ጅማ አባቡና ለፍፃሜ ተፋላሚ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በቅድሚያ 8 ሰዓት የተገናኙት ሰበታ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን ሲሆኑ በመጀመሪያው አጋማሽ ሰበታ ከተማ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች አሸነፈው ወጠዋል፡፡ በአጫጭር ኳሶ መሀል ሜዳ ላይ ጥሩ የኳስ ቅብብል በተስተዋለበት በዚህ ጨዋታ ሰበታ ከተማ ተጭነው በመጫወት ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረግ ችለዋል፡፡
በ9ኛው እና በ39 ደቂቃ ላይ ጥሩ ሆኖ የዋለው አብይ ቡልቲ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ለዋንጫው ጨዋታ እንዲደርሱ የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
★ፎቶ አብዬ ቡልቲ
በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ከመጀመሪያው አጋማሽ በወረደ አቋም ሲጫወቱ ተስተውለዋል ፡፡ በዚሁ በመጀመሪያው 45 በተቆጠሩ ሁለት ግቦች ሰበታ ከተማ 2-0 በሆነ ውጤት ኢትዮጵያ መድህንን መርታት ችለዋል፡፡
10:10 ሲል በርካታ ደጋፊዎች በታደሙበት የጅማ አባቡና እና የለገጣፎ ከተማ ጨዋታ ጠንካራ የመሸናነፍ ፍክክር በታየበት ፍልሚያ ጨዋታው ሊጠናቀቅ በ86 ኛ ደቂቃ ላይ የጅማ አባቡናው ጀሚል ያእቆብ ባስቆጠራት ጎል ቡድኑን ለእሁዱ የፍፃሜ ጨዋታ ማደርስ ችሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
አራት ቡድኖች በሚሳተፉበት የኦሮሚያ ዋንጫ በነጥብ የተሻሉት 1እና2 የሆኑ ቡድኖች ለዋንጫ ሲፋለሙ፤3ኛ እና 4ኛ ሆነው ያጠናቀቁ ቡድኖች ደግሞ ለደረጃ እሚጫወቱ ይሆናል፡፡
በዚሁ መሠረት በደረጃ ሰንጠረዥ መሰረት እና በነጥብ እና በጎል ክፍያ ለዋንጫ እና ለደረጃ እሚጫወቱ ይሆናል
ክለብ ተጫወተ ጎ/ል ነጥብ
1.ሰበታ ከተማ 3 2 5
2. ጅማ አባቡና 3 1 5
3.ለገጣፎ ከተማ 3 0 4
4.ኢት.መድህን 3 -3 1
እሁድ ጥቅምት 19 ቀን 2009
በ8:00 ሰዓት ለደረጃ
ለገጣፎ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድህን
በ 10:00 ሰዓት ለዋንጫ
ሰበታ ከተማ ከ ጅማ አባቡና እሚፋለሙ ይሆናሉ
#በሰበታ እስታዲየም