የኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ በተለያዩ የህትመት ጋዜጦች ላይ በዋና አዘጋጅነት ላለፉት 23 ዓመታት ሲሰራ የቆየው ታዋቂው የስፖርት
ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ግርማ በቅፅል ስሙ አልፈርጊ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በህመም ምክንያት በየካቲት ሆስፒታል ውስጥ ሆኖ ሲታከም ከቆየ በኃላ በተወለደበት የደብረ ብርሃን ከተማ ህይወቱ አልፏል፡፡
የኢትዮጵያ የስፖርት ታሪክ ውስጥ የህትመት ሚዲያዎች ከነበሩት ውስጥ በሻምፒዮና በማራቶን በአቴና የስፖርት ጋዜጦች ላይ ይሰራ የነበረ ሲሆን እስከ ቅርብ ሳምንት ድረስም በሊግ ስፓርት በሀትሪክ ስፖርት ጋዜጦች ላይ ይሰራ ነበር በተለይ ደግሞ በባህር ማዶ የስፖርት ዘገባዎቹ ላይ ይታወቅም ነበር፡፡
የታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ህልፈት ብዙዎችን ያሳዘነ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱ ነገ በደብረ ከተማ ይፈጸማል፡፡