በአመቱ መጀመሪያ ወደ ክለቡ የመጡቱ አሰልጣኝ ኒቦሳ ቩሲቪች በክለቡ በቆዩባቸው ጊዜያቶች በሊጉ ከ9 ጨዋታዎች መካከል ማሸነፍ የቻለው ሁለት ጨዋታዎችን ብቻ ነበር፡፡
ክለቡ አሰልጣኝ ኒቦሳ ቩሲቪችን ማሰናበቱን በፌስቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡አሰልጣኙ ከሀላፊነታቸው ለመነሳት እንደ መክንያት ሊሆን የቻለው የቡዱኑ ውጤት ማጣት ነው፡፡
ኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኙ የተነሰቡበትን ዋና ምክንያት በቀጣይ ቀናት እንደሚገልፅ በይፋዊ ፌስ ቡክ ገጹ ተናግሯል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ተሰናባቹ አሰልጣኝ ኒቦሳ ቩሲቪችን ተክተው ረዳት አሰልጣኝ ገዛኸኝ ከተማ እና ከ20 ዓመት በታች ቡድን አሰልጣኝ እድሉ ደረጄ በጊዜያዊነት ቡድኑን ይመሩታል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ማክሰኞ 11:30 ላይ ሃዋሳ ከተማን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ያስተናግዳል፡፡