በዝውውር መስኮት ላይ በንቃት እየተሳተፈ ሚገኘው ወልዋሎ የመሃል ሜዳውን ለማጠናከር ኣስራትን ከደደቢት ይሁንን ከጅማ ኣባጅፋር ማስፈረም ችለዋል።
ኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ31 ዓመታት በኃላ ወደ ኣፍሪካ ዋንጫ ሲመለስ መሃል ሜዳውን በብቃት የመራው ኣስራት በቀጣይ የቢጫዎቹን መሃል ክፍል የመምራት ሃላፊነት ይጠበቅበታል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ፕሪመርሊግ ኣሸናፊው ይሁን እንደሻው የፀጋይ ኪዳነ ማርያም ቡድንን ወልዋሎን በመቀላቀል የወልዋሎ የለውጥ ጉዞን ኣስቀጥሏል።ዋንጫ ባነሳው የጅማ ቡድን መሃል ሜዳ ላይ ከኣሚን ነስሩና ዮናስ ገረመው ጥሩ ጥምረት የፈጠረው ይሁን እንደሻው በቀጣይ ዓመት የወልዋሎን የመሃል ክፍል ከኣስራት መገርሳ ጋር በመጣመር ይመራል ተብሎ ይጠበቃል።