የኡጋንዳ የእግር ኳስ ቡድንንና ደጋፊዎችን የጫነች ጀልባ በአልበርት ኃይቅ ስትጓዝ ከ30 ሰዎች ጋር የመስመጥ አደጋ ገጠማት፡፡
ጀልባዋ ከአቅም በላይ ጭና በመጓዟ በአልበርት ሀይቅ ውስጥ መስመጧን የኡጋንዳ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በወቅቱ ጀልባዋ 45 ሰዎችን ጭና በመጓዟ እና ሚዛኗ ወደ አንድ ወገን በማጋደሏ ልትገለበጥ መቻሏን ነው ፖሊስ የገለፀው፡፡ አደጋው ከተከሰተ በኋላ 15 ሰዎችን በህይወት ማዳን መቻሉን የገለፀው ፖሊስ፣9 አስክሬን ደግሞ ከሀይቁ ወስጥ ማውጣት ማቻሉ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል፡፡
የስፖርተኞቹ ቡድን በገና በአል እለት ከሌላ አቻ የእግር ኳስ ቡድን ጋር ሊገጥም ይጓዝ እንደነበር ተገልጿል፡፡