የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
ሁለት ሳምንታትን እረፍት ላይ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚካሄዱ ሁለት ጨዋታዎች ይጀመራል፡፡
በሁለተኛ ዙር የሊጉ ጨዋታ መጀመሪያም ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ይደረጋሉ፡፡
በዛሬው ጨዋታም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወልድያ ከተማ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡
በሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዲስ አሰልጣኝ የሁለተኛ ዙር የሊግ ጨዋታውን ይጀምራል፡፡
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወልድያ በመጀመሪያው ዙር የሊጉ መርሃግብር ባደረጉት ጨዋታ ወልድያ 1 ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል፡፡
ሌላው በዛሬው ዕለት የሚካሄደው ጨዋታ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጅማ አባ ቡናን 11 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚገጥምበት ነው፡፡
ሁለቱ ክለቦች በውድድር ዘመኑ አንደኛ ዙር ጅማ ላይ ባደረጉት ግጥሚያ ባዶ ለባዶ መለያየታቸው ይታወቃል፡፡