ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በሁለት ምድብ ተከፍሎ 32 ክለቦች ሲሳተፉበት የቆየው የከፍተኛ ሊግ ውድድር በትናንትናው እለት በጅማ ከተማ አሸናፊነት ፍፃሜውን አጊኝቷል፡፡
ጅማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ አሸነፊ ሲሆን የመሸነፊያዋን ጎል በፍፁም ቅጣት ምት ማስቆጠር የቻለው የጅማ ከተማው የአጥቂ መስመር ተጨዋቾች አቅሌሲያስ ግርማ ሲሆን ስለ ጨዋታው እና ከክለቡ ጋር ስላለው ቆይታ ከሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል፡፡
ጨዋታውን እንዴት አገኘኸው?
አቅሌሲያስ:-ጨዋታው በጣም ደስ የሚል ነበር ተደራራቢ ከሆኑ የነጥብ ጨዋታወችን አልፈን ያደረግነው የክብር ጨዋታ ነበር ይህንን ጨዋታ እንደቡድን ተንቀሳቅሰን በብቃት በማሸነፋችን ደሰተኛ ነኝ በጨዋታው የማሸነፊያውን ጎል በማስቆጠሬም በጣም ደስ ብሎኛል።
በጅማ ከተማ ስለሚኖረው ቆይታ ተጠይቆ
- ማሰታውቂያ -
አቅሌሲያስ :- ከጅማ ከተማ ጋር ለአንድ አመት ነበር ኮንትራቴ እስካሁን አዲስ ነገር የለም ወደፊት አዲስ ነገር የሚኖር ከሆነ አብረን እናያለን ብሏል::