«የእናንተ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሆኑት ዲኤስቲቪ እና ሱፐር ስፖርት
ሰንዳውንስ ምን እየሰራ እንዳለ ለማወቅ ችለናል፡፡ በመሆኑም
በጨዋታው ላይ እኔ ምንም ያስደነቀኝ ነገር የለም፡፡»
ጋዜጠኛው አሰልጣኝ ማርት ኖይ በ2012 ከኬፕታውን ሳንቶስ ጋር
መቆየታቸው እና የደቡብ አፍሪካን አብሳ ፕሪሚየር ሺፕን ማወቃቸው
ለጨዋታው እንደረዳቸው ሲጠይቃቸው አሰልጣኝ ማርት ኖይ
የመለሱት እንዲህ በማለት ነበር፡፡
«በሚገባ ረድቶናል፤ ነገር ግን ላለፉት 17 አመታት አንስቶ እስከ አሁን
ድረስ በአፍሪካ ውስጥ ነኝ፡፡ በ6 አገራት በአሰልጣኝነት ሰርቻለሁ፡፡
በመሆኑም ተጨዋቾቼ ካላቸው የኢንተርናሽናል ጨዋታ ልምድ የተሻለ
እኔ አለኝ፡፡ በዚህም ምክንያት የተነሳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ
እኔን መርጦኛል፡፡ እኔም ደስተኛ ነኝ፡፡»
እኔ ሆላንዳዊ አሰልጣኝ ነኝ፡፡ በእኛ የአሰልጣኝነት ትምህርት ውስጥ
የጨዋታ ትንተና በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በመሆኑም ከራሴ ሰዎች ጋር
በመሆን ከጨዋታው በፊት የሰንዳውንስን ጨዋታ መርምሬያለሁ፡፡ እኛ
ለእያንዳንዱ ጨዋታ የራሳችን ሰው እንልካለን፡፡ በመሆኑም በቱኒዝ
የራሳችን ሰው አለን፡፡
ጋዜጠኛው ይቀጥላል፡፡ ከጨዋታው ፍጻሜ በኋላ በእናንተ የመልበሻ
ክፍል ውስጥ የሚሰማው ደማቅ የደስታ አገላለጽ ያልጠበቃችሁትን
ውጤት ማሳካት እንደቻላችሁ የሚያሳይ ነበር፡፡
«ይህ የአቻ ውጤት ለእኛ ድል ነው፡፡ የተጫወትነው ኳስን በአጭር
ቅብብል እና በፍጥነት ከሚጫወት ቡድን ጋር ነው፡፡ ይህንን እኛ
በአገራችን ውስጥ መጠቀም አለመድንም፡፡ በመሆንም ይህ ለእኔ
ተጨዋቾች ትልቅ ልምድ ይሆናቸዋል፡፡»
«በመሆኑም ሰንዳውንስን ማቆም በመቻላችን እና ይህ
አጨዋወታችንን ሊሰበሩ ባለመቻላቸው ኩራት ይሰማኛል፡፡ በእኔ
አመለካከት ቅርጻችንን ጠብቀብ እና በጣም ተደራጅተን
ተጫውተናል፡፡»
Source-የፈረሰኞቹ ገፅ