11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ ውሏል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም የሊጉ መሪ የሆነውን አዳማ ከተማን ያስተናገደው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታውን በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ችሏል።
ዛሬ ከ9 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ከተማን 2ለ0 በሆነ ውጤት ጨዋታውን በበላይነት አጠናቋል።
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሸናፊነት ጎሎችን ፒተር ኑዋዲንኬ በ19ኛው ደቂቃ እንዲሁም ፍቅረእየሱስ ተክለብርሃን በ57ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፈዋል።
- ማሰታውቂያ -
በዛሬው ጨዋታ አዳማ ከተማ የሊጉን መሪነት በሰፋ የነጥብ ልዩነት ለመያዝ ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀርቷል።
እሁድ ሊጉ ቀጥሎ 9 ሰዓት ላይ አራት ጨዋታዎች የሚስተናገዱ ሲሆን ደደቢት ከመከላከያ፣ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ጅማ አባ ቡና ከኢትዮጵያ ቡና እንዲሁም አርባምንጭ ከተማ ከፋሲል ከተማ ይጫወታሉ።
ወልድያ በአዲሱ ሼህ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ከድሬዳዋ ከተማ ጋር እሁድ 11 ስአት ላይ ጨዋታውን ያደርጋል።
የሊጉ 11ኛ ሳምንት የመዝጊያ ጨዋታ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወላይታ ዲቻን የሚገጥምበት ይሆናል።
ሊጉን አዳማ ከተማ በ10 ጨዋታ 21 ነጥብ በመያዝ ሲመራ በነገው እለት የ11ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን የሚያደርጉት ቅዱስ ጊዮርጊስ በ20፤ ደደቢት በ19 ነጥብ ይከተላሉ። ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን ጌታነህ ከበደ በ10፣ አዳነ ግርማ በ5፣ ሳላዲን ሰይድ፣ገብረሚካኤል ያዕቆብ፣ ፍሬው ሰለሞንና ሌሎችም በ4 ጎሎች ይከተላሉ።
1 አዳማ ከተማ 11 4 21
2 ቅዱስ ጊዮርጊስ 10 12 20
3 ደደቢት 10 7 19
4 ፋሲል ከተማ 9 6 18
5 ሲዳማ ቡና 11 1 18
6 አርባምንጭ ከተማ 10 2 16
7 ወላይታ ድቻ 9 2 15
8 መከላከያ 10 -1 15
9 ኢትዮጵያ ቡና 10 -2 13
10 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 10 0 12
11 ወልድያ 10 -3 10
12 ጅማ አባ ቡና 10 -4 9
13 ድሬዳዋ ከተማ 10 -6 9
14 ኢትዮ ኤሌክትሪክ 10 -4 7
15 ሀዋሳ ከተማ 9 -6 6
16 አዲስ አበባ ከተማ 11 -8 5
————————————————————
ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች
ደረጃ ተጨዋች ጎል
1 ጌታነህ ከበደ 10
2 አዳነ ግርማ 5
3 ሳላዲን ሰኢድ 4
4 ፍሬው ሰለሞን 4
5 ገብረሚካኤል ያዕቆብ 4
6 ኤዶም ሆሮሶውቪ 4
7 ወንድሜነህ ዘሪሁን 3
8 ፒተር ኑዋዲኬ 3
9 ምንይሉ ወንድሙ 3
10 አራፋት ጃኮ 3
11 ፍፁም ገብረማርያም 3
12 ሐብታሙ ወልዴ 3
13 አቡበከር ሳኒ 3
14 ሙጂብ ቃሲም 3
15 በዛብህ መለዮ 3