በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ የሶስተኛ ሳምንት መርሀ ግብር መሰረት ወደ አርባምንጭ ያመራው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ 3 ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል፡፡ በ13 ደቂቃ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ኤሌክትሪክን የተቀላቀለው አልሀሰን ካሉሻ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ቀዳሚ ማድረግ ሲችል፣ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሲል ላኪ ሳኒ አዞዎቹን በአቻ ውጤት ለእረፍት እንዲወጡ አስችሏል፡፡ ከእረፍት መልስ ተጨነው መጫወት የቻሉት አዞዎቹ በገብረሚካኤል ያእቆብ፤በላኪ ሳኒ ጎል የማግባት ሙከራዎች ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ በ54ኛ ደቂቃ በሲቲ ካፕ ውድድር ጥሩ ግልጋሎት ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ እየሰጠ እሚገኘው ዲዲየር ሊብሬ ሁለተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡ በዚሁ የ2-1 ውጤት አዞዎቹ በሜዳቸው ሽንፈትን ሊያስተናግዱ ችለዋል፡፡
——————————————————————
ሌላው በተመሳሳይ ሰዓት የተደረገው በሶዶ ስታዲየም አዳማ ከተማ ን ያስተናገደው ወላይታ ድቻ በሜዳው የ2-1 ሽንፈትን ሊያስተናግድ ችሏል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ጨዋታ በሜዳቸው ከደደቢት ጋር ነጥብ ተጋርተው የወጡት አዳማ ከተማዎች:: በመሀል ክፍል ተጫዋቻቸው ከነዓን ማርክነህ ሁለት ወሳኝ ጎሎች ሶስት ነጥብ ይዘው መመለስ ሲችሉ፡፡ለወላይታ ድቻ ቡዱኑን ከሽንፈት ያልታደገችውን ጎል በ52ኛ ደቂቃ ላይ ጃኮ አራፋት ማስቆጠር ችሏል፡፡
እንዲሁም ፋሲል ከተማ ወደ ጅማ አጅፋር አምርቶ ነጥቡን አሳክቶ መመለስ ሲችል፡፡
ለፋሲል ከተማ በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ለሁለተኛ ግዜ በመመጣት ለአፄዎቹ የፈረመው ፍሊኘ ዳውዚ ባስቆጠራት ግብ አፄዎቹ ወሳኝዋን ሶስት ነጥብ ማሳካት ችለዋል፡፡
—————————————————————–
የደደቢት ከ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ሪፖርት ሊንኩን ይጫኑ
——————————————————————