ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማክሰኞ ገበያ ላይ
በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? ሀትሪክ በማክሰኞ እትሟ ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ይዛሎት ከምትቀርበው ዘገባ መካከል በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን ባተረፈችበት THE BIG INTERVIEW አምዷ የቀድሞ የብሔራዊ ቡድናችን እና የተለያዩ ክለቦችን በማሰልጠን የሚታወቁት እንደዚሁም ደግሞ በትምህርታቸው የእግር ኳስ ኤክስፐርት የሆኑት አቶ ጌታሁን ገብረ ጊዮርጊስ በኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው ጊዜ ከ31 ዓመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ስላለፍንበት ጉዳዮች ዙሪያ እንደዚሁም ደግሞ በ1990 ስለተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ፎርማት እና ሌሎች ጥያቄዎች ተነስቶላቸው ምላሽን ለጋዜጣው ሰጥቷል፤ ምን ብለው ይሆን?
ሀትሪክ ስፖርት በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ በወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ኢትዮጵያ ቡናን ቡዙዋኖች ባልጠበቁት መልኩ ድል ስላደረጉበት ጨዋታ የቡድኑ ተጨዋች እና አንዷን የድል ጎል ያስቆጠረው ዮናስ በርታ ስለጨዋታው፣ ስለ ድሉ፣ ጎል ስለማስቆጠሩና የጎሏንም ማስታወሻነት በክቡር ትሪቩን ለሚገኘው እና የቄራ ልጅ ለሆነው አድናቂው ስለማድረጉ እንደዚሁም ደግሞ በእሁዱ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ቡና ወገን በጣም ስላስቸገራቸው አቡበከር ናስር የሚላችሁ ይኖራል፤ ከዛ ውጪ ደግሞ ሀትሪክ የምታስነብባችሁ ዘገባ የቅ/ጊዮርጊስ እና የፋሲል ከነማን ጨዋታ አስመልክቶ የፋሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ በግጥሚያው ዙሪያና በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ እንደዚሁም የቡድኑ ደጋፊዎችን አስመልክቶ ለቀረበለት ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥቷል፡፡ የነገ ጋዜጣዎ ሀትሪክ ስፖርት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ስለ አርሰናሉ ሁለገብ ኮከብ ተጨዋች ሱዋሬዝ፤ የማንቸስተር ሲቲው ሰርጂዮ አጉዌሮ አርሰናልን ባሸነፉበት ጨዋታ ሀትሪክ ስለመስራቱና ክለቡን መልሶ ወደ ዋንጫው ፉክክር ስለመክተቱ፣ የማንቸስተር ዩናይትዱ ማርከስ ራሽፎርድ ለክለቡ የድል ጎል አስቆጥሮ ለራሱም ለክለቡም ታሪክ ስለማስፃፉ እና ሌሎችም በርካታ ዘገባዎችን ሀትሪክ ስለያዘች የነገው እትም ላይ ሁሉንም የሚያገኙ ይሆናል፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ማክሰኞ ገበያ ላይ በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃው ተወዳጇ እና ባለቀለሟ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ገበያ ላይ ስትውል ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
Hatricksport team