ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለታላቁ የረመዳን የፆም ወር አደረሳችሁ
ሀትሪክ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ታስነብቦት ይሆን?
በቅድሚያ የሀገር ውስጥ ዘገባዋን በጥቂት እናስመልክታችሁ ሀትሪክ ከፍተኛ ተወዳጅነት ባተረፈችበት THE BIG INTERVIEW አምዷ እንግዳ አድርጋ ያቀረበችው የመከላከያውን ተጨዋች ፍፁም ገ/ማሪያምን ነው፤ የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ምን ብሎ ይሆን?
“ክልል ላይ ማሸነፍ የሚያስገኘው 3 ነጥብ ሳይሆን 9 ነጥብ ነው” ሲል
በክለቦች ደጋፊዎች መሀል ያለው ዘረኝነት በጊዜ ካልቆመ ወደ ብሔራዊ ቡድን
እንዳይተላለፍ ሰግቻለሁ„ም ይላል፡፡
ሀትሪክ ነገ ከምታስነብቦት ሌላ ዘገባዎቿ ውስጥ የፕሪምየር ሊጉን አስመልክቶ ዋንጫ የማንሳት እድሉ ካላቸው ክለቦች መካከል ሁለቱ ተጨዋቾች የሚሉት አላቸው፤ የመቐለ 70 እንደርታው ያሬድ ሀሰን
“ዘንድሮ ብዙ ስለለፋን ዋንጫው የመቐለ 70 እንደርታ ነው” ሲል
የፋሲል ከነማው ሽመክት ጉግሳ ደግሞ
“መቐለ ካሉት ጠንካራ ግጥሚያዎች አንፃር የሊጉን ዋንጫ እኛ እናነሳለን”
በማለት ይናገራል፡፡
ሀትሪክ ከእነዚህ ዘገባዎች ባሸገርም
የቱርክ አየር መንገድ ኢትዮጵያ በዓለም የስፖርት አደባባይ ስሟ እንዲጠራ እያደረገ ስላለው ጥረትም መረጃን ጋዜጣችን ይዛሎት ወጥታለች፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምን ታስነብቦት ይሆን?
ስለ ካታላኑ ክለብ ባርሴሎና እና ስለ ምትሃተኛው
አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ መነጋገሪያ ስለሆኑበት ጥልቅ ዘገባ ያቀረብንሎት ሲሆንቮክ ኦሪሊጠናቀቅ የአንድ ሳምንታት
ጨዋታ በቀረው የእንግሊዝ
ፕሪምየር ሊግ ውድድር ዙሪያም ዋንጫውን ለማንሳት ትንቅንቅ ውስጥ ስለገቡት ቡድኖች ማንችስተር
ሲቲ እና ሊቨርፑል መረጃን ከመስጠት ባሻገር ሊቨርፑሉ ኒውካስልን ባሸነፈበት ጨዋታ ለቀዮቹ ነፍስ አዳኝ ስለነበረው ዲቮክ ኦርጊ እንዲሁም ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶና በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የማክሰኞና የረቡዕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ዙሪያ የምናስነብቦት ይሆናል፤ የነገው ሀትሪክ አታምልጦት፡፡