በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ቡድኑ እየቀላቀሉ የሚገኙት ሃዲያ ሆሳዕናዎች የግብ ጠባቂያቸውን ስንታየሁ (ሲንባስ) ውል አራዝመዋል ።
የሀድያ ሆሳዕናው ግብ ጠባቂ ስንታየሁ ለተጨማሪ አንድ አመት በሀድያ ቤት ለመቆየት መስማማቱ ተነግሯል ።
ከሆሳዕና ከተማ የተገኘው ይህ ተስፈኛ ግብ ጠባቂ ከዚህ በፊት በደደቢት ተስፋ ቡድን እንዲሁም ዋናው ቡድን ተጫውቶ እንዳሳለፈ ይታወሳል።