የ27ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዮር ሊግ ሁሉም ጨዋታዎች ነገ ሰኔ 9 እና 10/2010 ዓ/ም በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲዮሞች እንደሚካሄዱ መርሃ ግብር ቢያዝላቸውም በወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት በተያያዘ 2 ጨዋታዎች እንደማይካሄዱ ታውቋል፡፡
-ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከተማ በሜዳው ከኢትዮጵያ ቡና ጋር እሁድ 9:00 ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተገናኘ ጨዋታውን ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ጨዋታው እንደማይደረግና መሰረዙ የታወቀ ሲሆን የሀትሪክ ስፖርት ምንጮች ባገኙት መረጃም ወደ ሀዋሳ ያቀናው የኢትዮጵያ ቡና ልዑካን ቡድን አባላት ሀዋሳ ከመግባታቸው አስቀድሞ መንገድ ላይ ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
-ነገ 9:00 ላይ በቦዲቲ ስታዲዮም ወላይታ ዲቻ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታም በተመሳሳይ በፀጥታ ችግር ምክንያት መሰረዙ ታውቋል፡፡
የሁለቱ ጨዋታዎች በተስተካካይ መርሃ ግብር መቼና የት እንደሚካሄዱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የሚወስን ይሆናል፡፡
- ማሰታውቂያ -
✍ሌሎች ጨዋታዎች
☞ቅዳሜ ሰኔ 9 ቀን 2010
04:00 ፋሲል ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
04:00 ወልዲያ ከተማ ከ ጅማ አባጅፋር (አ/አ)
09:00 ድሬዳዋ ከተማ ከ ኤሌክትሪክ
10:00 ደደቢት ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
☞ እሁድ ሰኔ 10 ቀን 2010
09:00 መቐለ ከተማ ከ መከላከያ
09:00 አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
ለሌላ ጊዜ የተላለፉ
ሃዋሳ ከተማ ?-? ኢትዮጵያ ቡና
ወላይታ ድቻ ?-? ወልዋሎ አዲግራት.ዩ