በ 2010 የኢትዮጵያ ፕሪመርሊግ ድንቅ ኣቋም ያሳዩት መቐለ ከተማዎች ቡድኑን በፋይናንስ ለማጠናከር የሚያግዘው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ከራያ ቢራ ጋር ተፈራርሟል።ውሉ ለሦስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በውሉ መሰረት መቐለ ከተማ በየዓመቱ 10 ሚልዮን ብር ሚያገኝ ይሆናል።በውሉም መሰረት መቐለ ከተማ በሚያደርጋቸው ስፓርታዊ እንቅስቃሴዎች የራያ ቢራን ምርት ሚያስተዋውቅ ይሆናል እነዚህም የማልያ ላይ ማስታወቅያ፣ቴሌቪዝን ስርጭት ማስታወቂያ እንዲሁም የፖስተር ማስታወቂያዎች ይገኙበታል።