የ2011 ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኖቹ መቐለ 70 እንደርታ 5 ተጨዋቾን ማስፈረማቸው ታውቋል።
የፊታችን ነሐሴ 5 በካፍ እፍሪካ ቻምፒዮንስ ሊግ የኢኳቶሪያል ጊኒውን ካኖ ስፖርት ሚገጥሙት መቐለዎች ኤፍሬም እሻሞን ከወልዋሎ፣ታፈሰ ሰርካን ከመከላከያ፣ፅዮን መርዕድና አለልኝ አዘነ ከእርባምንጭ ለማስፈረም ተስማምቷል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከወልዋሎ ጋር ጥሩ ሚባል ጊዜ ያሳለፈው የቀድሞ የሐረር ቢራ፣ኢትዮጵያ ቡና፣ንግድ ባንክና ደደቢት እማካይ ኤፍሬም እሻሞ የገብረ መድህን ሃይለን የማጥቃት ክፍል ሊያጠናክር እንደሚችል ይገመታል።
- ማሰታውቂያ -
የእርባምጭ ኣካዳሚ ውጤት የሆኑት ግብ ጠባቂው ፅዮን መርዕድና የመሃል እማካኙ እለልኝ እዘነ እንዲሂም ወደ ከፍተኛ ሊግ ከወረደው መከላካያ የመስመር ተከላካዩ ታፈሰ ሰርካ ሌሎች መቐለ 70 እንደርታን ለመቀላቀል የተስማሙ ተጨዋች ናቸው