በያዝነው ውድድር ዓመት ተደጋጋሚ ሽንፈቶችን ያስተናገደው መከላከያ ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር ተለያይቷል ።በክረምቱ ዝውውር መስኮት በርካታ ጥራት ያላቸውን ተጨዋቾችን ማስፈረሙን ተከትሎ ለዋንጫ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ የተገመተው መከላከያ ጉዞው ተቃራኒ ሆኖ ወራጅ ቀጠና ላይ ተቀምጧል።
የተጨዋቾቹን ድጋፍ ማግኘት ያልቻለው ስዩም ከበደ አጥቅቶ ሚጫወት ቡድን መስራት ቢችልም ቡድኑ መከላከል ላይ ደካማ መሆኑ ለውጤት መጥፋቱ በቀዳሚነት ሚጠቀስ ምክንያት ነው።
18 ነጥቦችን በመያዝ 14ተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው መከላከያ ቀጣዮቹን የሊግ ጨዋታዎች በምክትል እሰልጣኙ ምንያምር ፀጋዬ እየተመራ እሚያደርግ ይሆናል።