የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስና የኡጋንዳ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በቅርቡ ከግብጹ ዛማሌክ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ወደቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያመሩ ይመስላል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የክለቡን ጨዋታ የተመለከቱት ሚቾ ክለቡን ከተረከቡ የውጤት ቀውስ ውስጥ ያለውን ክለብ ሊታደጉት ይችላሉ።
ከክለቡ ጋር በርካታ ድሎችን ማጣጣም የቻሉት ሚቾ ለክለቡ ከፍተኛ ፍቅር እንዳላቸው በበርካታ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተገኙበትም ወቅት በደጋፊው ከፍተኛ እቀባበል ተደርጎላቸዋል።
- ማሰታውቂያ -