በአትዮጵያ ፕሪሜርሊግ 7ተኛ ሳምንት ሐዋሳ ከተማ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን እያደር እንደ ወይን እየጣፈጠ በሚገኘው በአንጋፋው ተጨዋቾች ሙሉአለም ረገሣ ጎል 1ለ0 አሸንፏል፡፡
በደጋፊዎች ዝማሬ የታጀቡት ባለሜዳዎቹ ሐዋሳ ከተማዎች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ነበራቸው በተደጋጋሚ ወደ ጎል መድረስ ቢችሉም ለግብ የቀረበ ሙከራ በማድረጉ ድሬዳዋ ከተማዎች ቀዳሚ ነበሩ ሀብታሙ ወልዴ በ15ኛ ደቂቃ ላይ በረጅሙ የተሻገረለትን ኳስ ከቅርብ ርቀት ሞክሮ ወደ ውጪ ስትወጣበት በጫዋታው ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ፍሬው ሰለሞን በተደጋጋሚ ለግብ የቀረቡ ሙከራዎች አድርጓል በተለይም በ24ደቂቃ በቀኝ መስመር ገፍቶ አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው አድኖበታል፡፡
በ32ደቂቃ ፍሬው ሰለሞን 16.50 አካባቢ ያገኘው ኳስ በግቡ አናት ላይ ሲሰዳት ይቺን ኳስ ለመመለስ የተወረወረው የድሬዳዋው ግብ ጠባቂ ሳምሶን አሰፋ ጉዳት አስተናግዶ ጫዋታዉ ለጥቂት ደቂቃዎች ተቋርጦ ከተጀመረ በሗላ ሳምሶን አሰፋ፡በጉዳት ከሜዳ ወጦ በምትኩ የቀድሞ የናሽናል ሴሜንት ግብ ጠባቂ ተመስገን ዳባ ወደ ሜዳ ተቀይሮ ገብቷል፡፡ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቆ ጭማሪ ደቂቃ ላይ ፍሬው ሰለሞን ከቀኝ መስመር አክርሮ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ተፍቶት የድሬዳዋ ከተማ ተከላካዮች ተረባርበው አውጥተዋታል፡፡የመጀመርያው አጋማሽም 0ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽ በ48ደቂቃ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ መድረስ የቻሉት ሐዋሳ ከተማዎች ዳዊት ፍቃዱ የመታውን ኳስ ግብ ጠባቂው ሲተፋው ያቡን ዊሊያምን ቀይሮ የገባው ሙላለም ረጋሳ ከመረብ አሳርፋታል፡፡ከግቧ መቆጠር በሗላ እንግዳዎቹ ድሬዳዋ ከተማዎች በረጅም የኳስ ቅብብል ወደ ግብ መድረስ ቢችሉም የተሳካ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም፡፡
በአንፃሩ ባለሜዳዎቹ በፍሬው ሰለሞን,ሙላለም ረጋሳ፤ፍቅረእየሱስ ተ/ማርያም፤ደስታ ዮሐንስ እና ዳዊት ፍቃዱ በተደጋጋሚ ወደ ግብ በመድረስ ጫና ፈጥረዋል፡፡ በ88ኛ ደቂቃ ላይ ፍቅረዕየሱስን ቀይሮ የገባው ፍርድአወቅ ሲሳይ ግብ አስቆጥሮ ከጫዋታ ውጪ ተብሎ ተሽሮበታል፡፡ ወዲያው በመልሶ ማጥቃት በግራ መስመር ዘላለም ኢሳያስ የመታት ኳስ የግቡን ቋሚ ታካ ልትወጣ ችላለች፡፡
የጨዋታው ሙሉ 90ደቂቃ ተጠናቆ ጭማሪ 4ደቂቃ ከታየ በሗላ በሐዋሳ ከተማዎች ማራኪ የኳስ ቅብብል ጫዋታው 1ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ-ሐዋሳ ከተማ
” በሜዳችን እንደ መጫዎታችን ነጥብ ይዘን ለመውጣት ነው የገባንው አጥቅተን ተጫውተን የግብ እድሎችን ፈጥረናል ተጋጣሚያችን በመከላከሉ ረገድ ጥሩ መሆናቸው እድሎችን እዳንጠቀም አድርጎናል፡፡ በተከላካይ መስመር ያለብንን ክፍተት ለመቅረፍ እንሰራለን፡፡”
አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው-ድሬዳዋ ከተማ
“በግብ ጠባቂ ስህተት ጎል ተቆጥሮብናል ሆኖም አጥቅተን ለመጫወት ጥረት አድርገናል፡፡ ነገር ግን አልቻልንም፡፡ በጉዳት ያጣናቸው ተጫዋቾች ክፍተት ፈጥረውብናል፡፡ ተጫዋቾቼ ሜዳው ከብዷቸው ነበር፡፡በቀጣይ ደካማ ጎናችንን ለማረም እንሰራለን፡፡”